1000072659

“አለቆቹዋ በጉቦ ይፈርዳሉ። ካህናቶቹዋ በዋጋ ያስተምራሉ። ነቢያቶቹዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ።  ት /ሚክያስ 3:10

የሶፎኒያስ ሌላኛዉ የሌብነት መልክ

ሀዋሳ በተለምዶ 05 ከሚባል ሰፈር የተከፈተ “ፕላቲኒየም” የሚባል ጭፈራ ቤት ዉስጥ “ቪ አይ ፒ” ክፍሉ ሌሎች ከስተመሮች እንዳይገቡ ተደርጎ አንድ ጉምቱ ባለስልጣንን እና ባለሀብትን ብቻ ታቅፏል፡፡ ከሁለቱ ፊት ለፊት ዉዱ “ብሉ” ዊስኪ ተከፍቷል፡፡ የሺሻ ማጬሻ  ዕቃዎችም ጭስ ይፍገመግምባቸዋል፡፡ ያለ ልክ ከተዘረጠጠዉ ቦርጩ ስብ ስር አስራዎቹን ያልጨረሱ አፍላ ኮረዶችን በግራና በቀኝ ያቀፉት ቱባዉ ባለስልጣን የቀድሞዉ ደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ የወቅቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሶፎኒያስ ደስታ ናቸዉ፡፡

ባለሃብቱ ባለስልጣኑን በዊስኪ የሚያጠምቁት ወዳጅነታቸዉ አስገድዷቸዉ ሳይሆን ለዓመታት ግንባታዉ መጠናቀቅ አቅቶት ሲንከባለል የመጣዉን የጬንቻን እና የላስካን የዉሃ ፕሮጀክት በቁርጥ ዋጋ ተደራድረዉ ለመዉሰድ የኮንትራት አስተዳደር ዉሉ በክልሉ ፍትህ ቢሮ በኩል ስለሚፀድቅ እርሱን ለማስፈፀም የቀረበ እጅ መንሻ ነዉ፡፡

እናም ጉዳዩ የቀረበላቸዉ “ሃላፊዉ” አቶ ሶፎኒያስ ምን ችግር አለዉ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ሆነ ምላሻቸዉ፡፡ አይ ድንገት ዓቃቤ ህጎቹ እንቢ እንዳይሉ በተለይ አንድ ዘዉዴ ለማ የሚባል ምክትል አለ በሚል ኮንትራክተሩ ስጋታቸዉን ሹክ ሲሉ “ኤዲያ ይኼ መድረሻዉ ያልታወቀ ስጋት ላይ ያለ አመራርና ሰራተኛ ምን ያመጣል ብለህ ነዉ”? ሆነ ምላሻቸዉ፡፡ በወቅቱ ክልሉ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበት እንደነበር ልብ በሉ፡፡

እናም ያን ምሽት ለዉስኪ፤ ለሺሻ/የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ የምሽት ጭፈራ ቤት ገብቶ ሺሻ ያጨሳል ብል የማታምኙስ ነገር/ እና ሌላ ሱሳ ሱስ ተጨምሮበት 73 ሺህ ብር ተከፍሎ በማግስቱ ሃላፊዉ ዉሉን ለማፀደቅ ከሌሎች ኃላፊዎች ጋር ቢሮ ዉስጥ የሸሚዛቸዉን እጅጌ ሰብስበዉ ለድብድብ መጋበዛቸዉን ሁሉም የቀድሞዉ የቢሮዉ ባልደረቦች ያዉቃሉ፡፡

ግብዣዉም፤ በጥሬ የወሰዱትም ብር ረብጣ ነበርና ሁለቱም ፕሮጀክቶች በመቶ ሚሊየኖች በሚቆጠር ብር ዉለታ ለዉስኪ ጋባዡ ኮንትራክተር ተሰጥቶ እነሆ እስከ ዛሬ ፕሮጀክቶቹ ባለስልጣናትን ዉስኪ እንጂ ምስኪኑን ህዝብ ዉሃ ማጠጣት ተስኗቸዉ እንደተንፏቀቁ አሉ፡፡

የፕሮጀክቶቹ ባለቤት፤ ዊስኪ ጋባዡ ኮንትራክተር ደግሞ ማን መሰላችሁ? ደቡብ ክልል ላይ ብቻዉን 17 ፕሮጀክቶችን በሞኖፖል የተቆጣጠረዉ የቀድሞዉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳዉ እህት ልጅ መልከኛዉና ሽቶ ተነስናሹ ፕሮጀክት ሳይት ሳይገባ ከግማሽ በላይ ክፍያ አየር ባየር የሚለቀቅለት የጥላሁን ከበደ ሸሪክ ምስክር ሃይለየሱስ ይባላል፡፡

ሌላው በባለፈው ክፍል 1 ባቀረብነው ዘገባ የመጨረሻውን ሀሳብ ለማስታወስ ያህል፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ደረት ኪሱ ላይ ሁሌም የማይለየዉ “መገጣጠሚያ ” ነዉ፡፡ “ለሚመለከተዉ ሁሉ” ብሎ አሊያም የተቋም ስም ክፍት አድርጎ ቀንና የደብዳቤ የወጪ ፕሮቶኮል ያልተሞላበት ደብዳቤ በብዛት ከመኪናዉ ዉስጥ አያጣም፡፡ ይህ ባህሪዉ በተለይ የቀድሞዉ ደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ እያለ የሰርክ ተግባሩ ስለመሆኑ ሁሉም ይመሰክራሉ፤ በየኮሪደሩም ያሙታል፡፡

ሚሊሻ የነበረዉን ሰዉ አንስቶ የደቡብ ክልል ፍትህ ምርምር ማዕከል ላይ የሆነ ቦታ ወሸቀዉ፡፡ ከዚያ ጎትቶት ፍትህ ቢሮ ጎለተዉ፡፡ ከዚያ እንዳሻዉ ያንደባልለዋል፡፡ እሰር፤ ፍታ፤ ክሰስ፤ ክስ አቋርጥ…….. ለሁሉም የጥላሁን ህቅታ ምላሹ እሺ ነዉ፡፡ በየመሸታ ቤቱ እንደሚያንቃርረዉ ጠርሙስ ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌለዉ ነዉና በዚህ ዕድሜዉ አሽከርነት አይሰለቸዉ እርሱ፡፡

አርባምንጭ ላይ የከተመዉን የክልሉን ፀረሙስና እንዲመራ የተሾመዉ ሶፎኒያስ ከኮሚሽኑ ይልቅ ባለጉዳይ የሚያስተናግደዉ እዚያዉ አርባምንጭ ከተማ ዉስጥ ራሱ በከፈተዉ ዊስኪ ቤት ነው። አዎ ሶፎኒያስ አርባምንጭ ዉስጥ ዊስኪ ቤት ከፍቶ ከባለጉዳዮቹ ጋር ለሌብነት ሲደራደር ትንሹ መስፈርት “ብላክ” ወይም “ጎልድ” ማዉረድ ነዉ፡፡ ከዚያ ወደ “ካሽ” ያድጋል፡፡

የዛሬ 7 ወር ገደማ የሶፎኒያስ መኪና ሹፌር እንደተለመደዉ አለቃዉን ቢሮዉ አስቀምጦ የመኪናዉን አፍንጫ ወደ ሶዶ አድርጎ ይከንፋል፡፡ በአለቃዉ ቶሎ አድርሰህ ተመለስ ተብሏልና ሹፌሩ ሩጫዉ ሌላ ነዉ፡፡ የሲዳማ ብሄር ተወላጁ ሹፌር በርካታ መሰል ስራዎችን ከዚህ ቀደም ሰርቷልና ወንጀሎች ሁሉ ለእርሱ ሙዝ የመላጥ ያህል ይቀሉታል፡፡

ልጁን ሲከታተል የነበረዉ ፌደራል ፖሊስ ግን የዛረዉን ጉዞ አክብዶበታል፡፡ ቁም ተባለ፡፡ አልቆምም ብሎ አሻፈረኝ አለ፡፡ ጥሶ ለመሄድም መንገድ ጀመረ፡፡ ፌደራል ፖሊሶቹም በጥይት እሩምታ መኪናዉን ከጢሻ ከተቱትና ተያዘ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሶፎኒያስ ደስታ መኪና ሲፈተሸ በህገወጥ የጦር መሳሪያ ሽጉጦች የታጨቀ፤ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን የጫነ ሆኖ ተገኘ፡፡ መኪናዉም ሹፌሩም በህግ ጥላ ስር ዋሉ፡፡ ስነምግባር የሌላቸዉ ኮሚሽነሩ ከሃላፊነታቸዉ ይነሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ የርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ቁጥር አንድ ላሽ አጎንባሽ ናቸዉና ዛሬም ድረስ “ኮሚሽነር” እየተባሉ እየተላላኩ አሉ፡፡ ….. ክፍል 3…4.. 5 ይቀጥላል! እያዝናናን ቁምነገር እናስጨብጣለን ከእኛ ጋር ይቆዩ 🙏