በዛሬው ዕለት ለዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች ተሸላሚዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በ2013 ዓ.ም የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትም/ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የትምህርት፣ ምርምር፣ የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከአጠቃላይ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል 2ኛ በመውጣቱ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች መካከል በአመራር ብቃት 1ኛ በመውጣታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ አቀባበል በአከባቢውና በዩንቨርስቲው ማህበረሰብ እንዲሁም በተማሪዎች ተደርጎላቸዋል።
በዛሬው ዕለት ለዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች ተሸላሚዎች በተደረገው አቀባበል የተጀመረው ከቦዲቲ ከተማ ጀምረው እስከ ሶዶ ከተማ የአከባቢውና የዩንቨርስቲው ማህበረሰብ፣ በመንግሥት አመራሮች እንዲሁም በተማሪዎች ተደርጓል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 11/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
