በዎላይታ ዞን ለጀግና መከላከያ ሠራዊት ሁሉንም ህብረተሰብ ለማነቃነቅ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ለንቅናቄው ሥራ በታቀደዉ መነሻ ዕቅድ ዙሪያ ዉይይት በዛሬው ዕለት መድረክ አካሂዷል።
በአሸባሪው ህወሃት የተቃጣብንን ጥቃት ለመመከት መላው የዞኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ ሴቶችንና ወጣቶችን በማነቃነቅ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋዖኦ እንዲያደረጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ማለትም የሞራል፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በተደራጀ መንገድ በመሰብሰብ እስከ ሠራዊቱ እንዲደርስ ማድረግ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
አሸባሪው ህወሃት በሀገራችን ላይ የከፈተዉ ጦርነት አሳፋሪ መሆኑንና ይህን የማክሸፍ እርምጃ እየወሰደ ላለው መከላከያ ሠራዊታችን የዞናችን መላው ህብረተሰብ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሰጡ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ንቅናቄ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ የዎላይታ ዞን አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኤርሚያስ ገልጸዋል፡፡
በሁሉም አካባቢ ከአሸባሪው ህወሃት የተቃጣብንን ትንኮሳና ግጭት ለመቋቋም የሚያስችል ህዝባዊ የሞራል እና ቁሳዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባት እንዳለበት አቶ አበባየሁ አሳስበዋል፡፡
በዞን ደረጃ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ ከ14 ሚሊዮን 9 መቶ ሺህ ብር በላይ ለማሰባሰብ የታቀደ መሆኑን ተገልጿል፡፡
ኢትዮጲያን አሬንጓዴ እናልብሳት ሀገራችንን ከጁንታው እናጽዳት ‘’ በሚል መሪ ቃል አረንጋዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ ቀርቧል፡፡
አሸባሪው ህወሃት በጀግናዉ መከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጥቃት መፈፀሙ እጅግ አስነዋሪ ድርጊት እንደሆነ ኮሚቴ አባላት አወግዘው የጦር መሣሪያን ከህፃናት ትከሻ መወረድ እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡
ሁሉንም ማህበራዊ መሰረት በማስተባበር የሀብት አሰባሰብ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግና ሴቶች፤ ወጣቶችንና የንግዱን ማህበረሰብ በአደረጃጀት በማስተባበር የድጋፍ ስልፍ በመውጣት እስከ ደም መለገስ ጭምር ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ የዎላይታ ዞን አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኤርሚያስን ጨምሮ ሌሎች የዞን እና የወረዳ/ከተማ አስተዳዳር ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል መባሉን ለዎላይታ ታምስ ሚዲያ ከደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1 በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 11/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹

