IMG_20251003_112844_438

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ በተደጋጋሚ አልቀበልም በማለት መፈጸም ሲያቅተው፣ ዛሬ በኃይል ተገዶ እንዲያስፈጽም መደረጉን WT Media ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የፌዴራል ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተሰጠው ከማራ ማይነርስ ባለቤት አቶ ብርሃነመስቀል ክንፈ ጋር በተያያዘ ለክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ የእግድ ትዕዛዝን አስመልክቶ ነው።

በዛሬው ዕለት ሁለት ሙሉ የፖሊስ ፓትሮል የጫኑ የፌዴራል ኮማንዶ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በኃይል ለማስፈጸም ወደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ደርሰዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው (በጥላሁን ከበደ እየተደረገ ያለውን የዎላይታን ሕዝብ በደል በዝምታ እየተመለከቱ የሚገኙ) የፌዴራል ፖሊስ ቢሮአቸው ሲደርስ “ስብሰባ ላይ ነኝ” በማለት ለመሸሽ ቢሞክሩም፣ ስብሰባውን አቋርጠው በአስቸኳይ እንዲመጡ ከፌዴራል ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

ኮሚሽነሩም ጥቂት ደቂቃዎችን እንዲጠብቁላቸው ጠይቀዋል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 337812 የሰጠው ግልጽ ትዕዛዝ ቢኖርም፣ የክልሉ መንግሥት ትዕዛዙን ባለመቀበል ሕግን ሲጥስ ቆይቷል።

ፍርድ ቤቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ እግዱን እንዲያከብሩ እና እንዲያስፈጽሙ አዟል።

በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ፣ የጋሞ ዞን ፖሊስ፣ የቦረዳ ወረዳ ፖሊስ ይህንን የእግድ ትዕዛዝ እንዲከበር ጥብቅ ክትትልና እንዲፈጸም የማድረግ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የማራ ማይነርስ ባለቤት አቶ ብርሃነ መስቀል በክልሉ ውኃና ማዕድን ቢሮ ውስጥ የሚፈጸመውን ብልሽት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዲጋለጥ በማድረጉ ቂም ይዘው፣ የክልሉን የፍትህ ተቋማት (ም/ኮሚሽነር ጉራማይሌን ጨምሮ) በመጠቀም፣ ጉዳዩ በፌዴራል ፍርድ ቤት ክርክር ላይ እያለ ባለሀብቱን ሕግን ጥሰው አስረው እያሰቃዩ ይገኛሉ።

ትዕዛዙን ለመስጠት የመጡት የፌዴራል ፖሊሶች ከዚህ ቀደም እንዳረጋገጡት፣ ባለሀብቱ እንዲታሰሩ ከተደረገ በኋላ፣ በርዕሰ መስተዳድሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በክስ ሂደት ላይ ባለው የማዕድን ቦታ ላይ ከአምስት በላይ ድርጅቶች ገብተው እየሰሩ እንደሚገኙ ታውቋል።

ይህ የፌዴራል የኃይል እርምጃ “ፍትህ በግፍ ለታሰረው ብርሃነመስቀል ክንፈ” የተሰጠ ምላሽ ሲሆን፣ ክልሉ የሕግ የበላይነትን ወደ ጎን በመተው ባደረገው እንቅስቃሴ ምክንያት በመንግሥት ላይ ያለውን የሕዝብ እምነት እያሳጣ መሆኑ ተጠቁሟል።

ድርጊቱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደና ተባባሪዎቻቸው “ሽንፈትና ውድቀት” መሆኑም ተመልክቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ WT Media በዝርዝር ዘገባ ይመለሳል።

Ethiopia #Wolaita #southethiopia