FB_IMG_1759682920685

ወቅታዊ መረጃ: የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፌዴራልን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዳግም ተቃወመ፤ የፈደራል ፖሊስ አባላት መንገላታት ገጠማቸው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ በተደጋጋሚ “አልቀበልም” በማለት መፈጸም ሲያቅተው፣ ትዕዛዙን በኃይል ለማስፈጸም ወደ ክልሉ የተላኩት የፌዴራል ፖሊስ ኮማንዶ አባላት ዳግም እክል እንደገጠማቸውና እየተንገላቱ መሆናቸውን WT Media ያገኘው ወቅታዊ መረጃ አመልክቷል።

ከሶስት ቀናት በፊት እንደዘገብነው፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወጣት ባለሀብቱ አቶ ብርሃነመስቀል ክንፈ (ከማራ ማይነርስ ባለቤት) እና በክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ መካከል በተፈጠረው ክስ ላይ የሰጠውን የእግድ ትዕዛዝ ለማስፈጸም ሁለት ሙሉ የፖሊስ ፓትሮል የጫኑ የፌዴራል ኮማንዶ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ክልሉ ውስጥ ደርሰው ነበር።

የኮሚሽነሩ መሸሽ: የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው (በዘገባው የአቶ ጥላሁን ከበደ ተላላኪ እንደሆኑ ተጠቅሷል) የፌዴራል ፖሊስ ቢሮአቸው ሲደርስ “ስብሰባ ላይ ነኝ” በማለት ለማምለጥ ቢሞክሩም፣ ስብሰባውን አቋርጠው በአስቸኳይ እንዲመጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ነበር።

አዲስ እንቅፋት: በዛሬው ዕለት የደረሰው መረጃ ግን የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ሶዶ ከተማ ላይ ለሶስተኛ ቀናቸው ተቀምጠው እንደሚገኙ ያመለክታል። የክልሉ መንግሥት የእግድ ትዕዛዙ ወደሚመለከተው የቦረዳ ወረዳ ሳይት እንዳይገቡ በማድረግ እየተገፉ መሆናቸው ተነግሯል።

ተደጋጋሚ እንቢተኝነት: የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት፣ ይህ የፌዴራል ፖሊስ መደናቀፍ አዲስ አይደለም፤ ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ መልኩ ሶስት ጊዜ ተመላልሶ የክልሉ መንግሥት እንቢተኛ ሆኖ መመለሱን ጠቁመዋል።

የክልሉ መንግሥት ይህንን ሕግ የማስፈጸም ፈቃደኛ አለመሆን ያሳየው፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 337812 የሰጠው ግልጽ የእግድ ትዕዛዝ እያለ ነው።

የፍትህ ተቋማት መጠቀሚያነት: ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ባለሀብቱ በክልሉ ውኃና ማዕድን ቢሮ ውስጥ የሚፈጸመውን ብልሽት በፋና ሚዲያ በማጋለጣቸው ቂም በመያዝ፣ የክልሉን የፍትህ ተቋማት (ም/ኮሚሽነር ጉራማይሌን ጨምሮ) በመጠቀም፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ እያለ ባለሀብቱን በሐሰት ክስ አስረው እያሰቃዩ ይገኛሉ።

  የሥልጣን አላግባብ መጠቀም: ባለሀብቱ ከታሰሩ በኋላ፣ በርዕሰ መስተዳድሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በክስ ሂደት ላይ ባለው የማዕድን ቦታ ላይ ከአምስት በላይ ድርጅቶች ገብተው እየሰሩ እንደሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም አረጋግጦ ነበር።

የመረጃ ምንጮች እንዳሉት፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ “ሕግ ለማስፈጸም መጥተው በክልሉ አብዲ ኢሌ ጥላሁን ከበደና በኮሚሽነር ፍስሀ ጋረደው ሴራ” ከሥራቸው ተስተጓጉለው መቀመጣቸው እንዳሳዘናቸው ተገልጿል። ይህ የፌዴራል ፖሊሶች መንገላታት በክልሉ የሕግ የበላይነት እንደሌለ ለማረጋገጥ አንዱ ማስረጃ ነው ተብሏል።

በአንባገነን እና ሙሰኛ መሪ እየተሰቃየ ያለዉ ክልሉ የፌዴራል መንግሥትን ልዩ ትኩረት ሊያገኝ እንደሚገባም ተጠቁሟል። የፌዴራል ፖሊሶች አሁንም ዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ተቀምጠው የክልሉን መንግሥት ሁኔታ እየተከታተሉ ይገኛሉ።

WT Media በጉዳዩ ዙሪያ የቅርብ ጊዜ ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረቡን ይቀጥላል።
#Ethiopia #southethiopia