#ሰበርዜና
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች በጎፋ ተጎጂዎች ስም ከተሰበሰበ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሸሽ ሲሞክሩ በፌዴራል ደህንነቶች ተይዟል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጎፋ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ወገኖች ከተሰበሰበው የእርዳታ ገንዘብ ውስጥ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሸሽ የተደረገው ሙከራ በፌዴራል የደህንነት አካላት መጋለጡን WT Media ከፌዴራል ደህንነት መዋቅር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ አሁን የደረሰው መረጃ የክልሉ አመራሮች ቀደም ሲል ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የእርዳታ ሀብት ለተጎጂዎች ሳይደርስ መመዝበሩን አስመልክቶ WT Media ከወራት በፊት የዘገበውን ስጋት የሚያጠናክር ነው።
በዛሬው ዕለት ለWT Media የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ይህንን የሙስና እና የዘረፋ ሥራ የጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ ናቸው።
የክልሉ ቁልፍ ባለሥልጣናት ከጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተክለማርያም በቀሌ ጋር በመቀናጀት ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሸሽ ከደላላ ጋር ተመሳጥረው ነበር።
የፌዴራል ደህንነቶች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጋራ በመተባበር ደላላውን በቁጥጥር ስር በማዋል ከአራት ቀን በላይ በሕግ ጥላ ስር አቆይተዋል።
የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተክለማርያም በቀሌ የባንክ ቼክ ማሻርያ ደብዳቤ በማዘጋጀት ወደ ሳውላ ንግድ ባንክ የማጭበርበር ሥራ ሲሰሩ በፌዴራል ደህንነቶች እጅ ላይ ደርሶባቸዋል።
ጉዳዩ ለሕዝብ እንዳይደርስና ቁጣ እንዳይቀሰቀስ ተፈርቶ ታፍኖ መቆየቱ ተገልጿል፤ ሆኖም WT Media በተጨባጭ የሰነድ ማስረጃዎችን ባደረገው ብርቱ ጥረት ማግኘት ችሏል።
የአሁኑ ሰዓት አቶ ተክለማርያም በቀሌን ከሕግ ለማሸሽና ለመሰወር በጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በኩል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።
ይህ ድርጊት የተፈጸመው በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ለማገዝ ከመላው ዓለም ከተሰበሰበው ድጋፍ እንደሆነ ታውቋል።
ቀደም ሲልም WT Media እንደዘገበው፣ በአደጋው ሰዓት ከተለያዩ አካላት የተሰበሰበው ከ600 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ ሀብት ለተጎጂዎች ሳይደርስ በክልሉ አመራሮች እንደተመዘበረ ተረጋግጦ ነበር።
በወቅቱ በዚህ የሙስና ቅሌት ውስጥ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ አቶ አክሊሉ አዳኝ እና አቶ ጋንታ ጋምኣ ስማቸው ተደጋግሞ በመነሳት ይጠቀሱ ነበር።
አመራሩ በሕዝብ ለቅሶና በሰው ደም የመነገድ ተግባር ውስጥ መግባቱ “የዘመናችን ነውረኛ ተግባር” መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ “አፈር በበላቸው ወገኖች ደም መቀለድ ለለመዱ” ባለሥልጣናት ሕግ ሊያስከብርላቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በአደጋው የተጎዱ ወገኖች አሁንም ቢሆን የቀይ መስቀልና ሌሎች ድርጅቶች ከረዷቸው ውጪ፣ በረሀብና በችግር እየተሰቃዩና እየተሰደዱ መሆናቸው ተገልጿል።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media
#Ethiopia #southethiopia #Gofa