የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ “12 ቢሊዮን ብር” ሙስና ክስ በባለሀብቱ ላይ በመመስረት ሪከርድ መስበር መቻሉ ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በአንድ ልማታዊ ባለሀብት ላይ “12 ቢሊዮን ብር” የሚገመት የሙስና ክስ በመመስረት በአገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ የክስ መጠን ሪከርድ መስበሩን WT Media ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ ክስ ቀደም ሲል በ1.4 ቢሊዮን ብር ተጀምሮ አሁን ወደ 12 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፣ በአገሪቱ ታሪክ ከመቶ ሚሊዮኖች ያልዘለለውን የሙስና ክስ ወደ ቢሊዮን ብር በማሻገር ከፍተኛውን ደረጃ ይዟል።
ለአብነትም የቀድሞው የሜቴክ እና የጥረት ኮርፖሬት ኃላፊዎችን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን እነዚህ ክሶች ከዚህ ቀደም ከመቶ ሚሊዮኖች ያልዘለሉ ወደ ቢሊዮን ብር ያልተሻገሩ ነበሩ።
አሁን ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይህንን ሪከርድ ሰብሮ “የ12 ቢሊዮን ብር” ክስ ይዞ ብቅ ብሏል።
የሚገርመው ደግሞ የሀገሪቱ የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ ከወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 ድንጋጌዎችን ባፈነገጠ መልኩ ከህግ አሰራር ውጪ ወንጀል ፈፅሟል የተባለው የመንግስት ባለስልጣን ሳይሆን ልማታዊ ባለሀብት መሆኑ እና ቀደም ብሎ በመንግሥት ሚዲያ በሆነው በፋና ቴለቪዥን “የማዕድን ስር ቁማር” በተሰኘው የምርመራ ዘገባ እንደተመለከትነው ወንጀል ፈፅመው ያየናቸው አካላት በፈፀሙት ወንጀል ራሳቸው ከሳሽ ሆነው እና ወንጀል የተፈፀመበት እና ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ ደግሞ ተከሳሽ የሆነበት መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
በዚህም የክሱ ሂደትና አፈጻጸም ግን የሕግ አሠራርን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው።
ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉት የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሠራተኞች ሳይሆኑ፣ ተከሳሹ የሆኑት ወጣቱ ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ናቸው።
እሳቸውም በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተደጋጋሚ እንደተዘገበው በሳውላ ማረሚያ ቤት ያለ ፍርድ ታስረው ይገኛሉ።
ጉዳዩ ከማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ቀደም ብሎ በፋና ቴሌቪዥን “የማዕድን ስር ቁማር” በሚል የምርመራ ዘገባ ወንጀል ሲፈጽሙ የታዩ አካላት ዛሬ ላይ ራሳቸው ከሳሽ ሆነው መቅረባቸው የፍትሕ መዛባትን ያሳያል።
በ12 ቢሊዮን ብር የሚገመተው ወንጀል ተፈጽሟል እየተባለ፣ በክሱ ውስጥ ተባባሪ ሆኖ የተከሰሰ ወይም በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ያለ አንድም የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ባለሥልጣን የለም።
ይህ ደግሞ ወንጀል የፈጸሙ የመንግሥት አካላት ከተጠያቂነት ለማምለጥ የፈጠሩት የሐሰት ክስ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል ተብሏል።
ይህ ሪከርድ የሰበረ ክስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምን ያህል ከሕግ አሠራር ውጪ የመንግሥት ሥራዎች የሚከናወኑበትና በግለሰቦች ጥላቻ እና ቂም በቀል ትዕዛዝ ፍትሕ የሚጓደልበት መሆኑን ያሳያል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም ወጣት ባለሀብቱ እንጂነር ብራሀነመስቀል በከፈቱት ክስ መዝገብ ላይ የፌዴራል ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማስፈጸም ወደ ክልሉ እንዳይገባ መከልከሉ፣ የክልሉ አመራሮች ወንጀላቸውን ለመደበቅ እና ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ክልሉ ከፌዴራል መንግሥት ትዕዛዝ ጭምር እንዳይገዛ እስከመድረስ መሄዳቸው በቂ ማሳያ ነው።
ክልሉን እንደ የግል ንብረት የሚዘውሩት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ ይህን የ12 ቢሊዮን ብር ክስ በማስመሰረት የፍትሕ ተቋማትን በመጠቀም የግፍ በቀል የሚፈጸምበት መሆኑን ክሱ አመላካች ነው።
ክሱ፣ ዜጎች ለመብታቸው መታገል የማይችሉበት፣ ሕገወጥነትን መታገል እና ወንጀሎችን ማጋለጥ ለቂም በቀል፣ ለሐሰት ውንጀላ እና ክስ የሚዳርግበት ክልል መሆኑን ያሳያል።
በትናንትናው ዕለት እንደዘግብነው የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ትዕዛዝ ለማስፈፀም ወደ ቦረዳ ወረዳ ሳይት እንዳይገቡ ተከልክለው ለሦስት ቀናት ያህል ዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ ተቀምጠው መንገላታት እንደገጠማቸው ይታወቃል።
የመረጃ ምንጮች ይህ የፌዴራል ፖሊስ መደናቀፍ አዲስ አለመሆኑንና ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ መልኩ ሶስት ጊዜ ተመላልሶ የክልሉ መንግሥት እምቢተኛ ሆኖ መመለሱን አስረድተዋል።
የክልሉ መንግሥት ይህንን ሕግ የማስፈጸም ፈቃደኛ አለመሆን ያሳየው፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ልደታ ምድብ 6ኛ ንግድ ይግባኝ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 337812 የሰጠው ግልጽ የእግድ ትዕዛዝ እያለ ነው። ትዕዛዙ የተሰጠው ከማራ ማይነርስ ባለቤት አቶ ብርሃነመስቀል ክንፈ ጋር በተያያዘ ነው።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ባለሀብቱ በክልሉ ውኃና ማዕድን ቢሮ ውስጥ የሚፈጸመውን ብልሽት በማጋለጣቸው ቂም በመያዝ፣ የክልሉን የፍትህ ተቋማት (ም/ኮሚሽነር ጉራማይሌን ጨምሮ) በመጠቀም፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ እያለ ባለሀብቱን በሐሰት ክስ አስረው እያሰቃዩ ይገኛሉ።
ባለሀብቱ ከታሰሩ በኋላ፣ በርዕሰ መስተዳድሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በክስ ሂደት ላይ ባለው የማዕድን ቦታ ላይ ከአምስት በላይ ድርጅቶች ገብተው እየሰሩ እንደሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም አረጋግጦ ነበር።
ይህ የፌዴራል ፖሊሶች መንገላታት “በክልሉ የሕግ የበላይነት እንደሌለ ለማረጋገጥ አንዱ ማስረጃ ነው” ያሉት የመረጃ ምንጮች፣ በአንባገነን እና ሙሰኛ መሪ እየተሰቃየ ያለው ክልሉ የፌዴራል መንግሥትን ልዩ ትኩረት ሊያገኝ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፌዴራል መንግሥት በክልሉ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ እና ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ ቀርቧል።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media