GridArt_20251008_195947572

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ ውስጥ በሐሰተኛ (ፎርጅድ) ደረሰኞች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን የመንግሥት ገቢ ተሰብስቦ መመዝበሩን WT Media ከወረዳው ያገኘው የሰነድ ማስረጃ ያመለክታል።

ይህ ከፍተኛ ምዝበራ የተፈጸመው ከማዕድን ገቢ (ሮያሊቲ) መሰብሰቢያ ደረሰኞች ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ የደረሰበት የሰነድ ማስረጃ እንደሚያመለክተው፣ የተሰበሰበበት ደረሰኝ በሕጋዊ መንገድ ወጪና ገቢ ያልተደረገ መሆኑ በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ተረጋግጧል።

በዚህ ሕገወጥ አሠራር ከ50 በላይ ጥራዞች ወይም ከ2500 በላይ ደረሰኞች ተጠቅመው ከተሰበሰበው ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተቀራምተውታል ተብሏል።

አቶ አሸናፊን ጨምሮ ወረዳውን ቀደም ብለው የመሩ አስተዳዳሪዎችም በሚሊዮኖች የሚቆጠር የሀብት ድርሻቸውን በማጭበርበር እንደተከፋፈሉ ተነግሯል።

እነዚህ የሐሰት ደረሰኞች ሌሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች የተዘረፉባቸው ሰነዶች ጭምር፣ ከማንኛውም ሕጋዊ አካላትም ሆነ ኦዲት እንዳይደረጉ ታግደውና ተቆልፎባቸው በድብቅ ሰነድ ክፍል ውስጥ ተቀምጠዋል።

ይህ የዘረፋ ቅሌት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች በቅርቡ በጎፋ የእርዳታ ገንዘብ ዘረፋ እና በወጣት ባለሀብቱ እንጂነር ብራሀነመስቀል ላይ 12 ቢሊዮን ብር የሙስና ክስ ዙሪያ በተደጋጋሚ ለሕግ እየቀረቡና እየተጠቀሱ ባሉበት ወቅት የተከሰተ ነው።

ይህም የክልሉን የሙስና አሠራር እና የሕግ የበላይነት መጓደል ምን ያህል ስር እየሰደደ መሆኑን የሚያሳይ ነውና የሚመለከተው አካል ምርመራ በማካሄድ የህግ ተጠያቂነትን እንዲያሰፍን ጥሪ እናቀርባለን።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media