GridArt_20251009_182036576

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራር በሴራ የተደራጀ መዋቅርን በመጠቀም ማተራመስና በመመዝበር ላይ – አሳዛኙ የጎፋ ዞን ተሞክሮ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ መዋቅሩን በሴራ በማደራጀትና የጥቅም መረብ በመዘርጋት ሌሎች ዞኖች መረጋጋት እንዳይችሉ እያደረጉ ነው ሲል ከከፍተኛ የጎፋ ተወላጅ ባለሥልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ( WT Media ) መረጃ ያመለክታል።

አቶ ጥላሁን ከበደ “በሁሉም ዞኖች ሁለት ተቃራኒ ቡድን” በማስፈጠር፣ ማታ ማታ ለራሱ ወገን ተልዕኮ በመስጠትና ጠንካራ የአካባቢ ልጆችን በማስጠቃት፣ ጠዋት ላይ ደግሞ መድረክ ላይ ቆሞ የክልሉን ስም “የሰላምና የብልጽግና ተምሳሌት ክልል” እያለ እንደሚሰብክ መረጃው ይገልጻል።

ከሴራው የተደራጀ ስቃይ ላይ ካሉ ዞኖች አንዱ ጎፋ ዞን ነው። ዘገባው የጎፋ ሕዝብ በሙሉ እውነተኛ ነፃነትና ልማት የሚገኘው “አቶ ጥላሁን ከክልሉ ሲወጣ ብቻ” እንደሆነ እንደሚገነዘብ ይጠቁማል።

የጎፋ ዞን አመራር አደረጃጀት ሆን ተብሎ የተሳሳተ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ አቶ ጥላሁን ከበደ “አቶ ተስፋ እጅ ከገባ ከእጅ ይወጣል” በሚል አስተሳሰብ ምንም ዓይነት ዕውቀትና አቅም የሌለው፣ ለራሱ ብቻ ታማኝ የሆነና የጎፋ ሕዝብ ጠላት የሆነውን አቶ ዳግማዊ አየለን በዋና አስተዳዳሪነት አስቀምጠዋል።

የጎፋ ዞን አመራሮች በኬንቾ ሳቻ ጎዝድ ቀበሌ የተፈጠረውን አስከፊ አደጋ “እንደ ምቹ ዕድል” በመጠቀም ከተሰበሰበው የእርዳታ ገንዘብ ከፍተኛ መጠን መደበቁ ተገልጿል።

ከክልልና ከፌዴራል ተቋማት ቃል የተገባው ገንዘብ (ከ210 ሚሊዮን ብር በላይ ተፈቅዷል፣ ከ145 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ክልሉ አካውንት ገቢ ሆኗል) ለተጎጂዎች ሳይውል ቀርቷል።

መረጃው እንደሚለው፣ ይህንን ገንዘብ ይመራል የተባለው የአቶ ጥላሁን ታማኝና “ቡቺላ” የሆነው ጡረተኛ ሽማግሌ አቶ ጋንታ ጋምኣ ነው።

አቶ ጋንታ ጋምኣ “ለሆድ ከተባለ አይደለም አካባቢ ሚስቱንና ልጁን ይሽጣል” እስከመባል የደረሰ ግለሰብ ሲሆን፣ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በፈጠረው “ጋብቻ” የጎፋ አካባቢ ተወካዮች የገባውና የወጣው ገንዘብ እንኳን መገምገም እንዳይችሉ ተደርጓል።

በክልል ደረጃ አቶ ጥላሁን እና አቶ ጋንታ ገንዘቡን ሲከታተሉ፣ በዞን ደረጃ አቶ ዳግማዊ፣ አቶ ተክሌ (ተክለማርያም) እና አቶ ማርቆስ (መለሰ) ክትትሉን ያደርጋሉ። ሌሎች ካድሬዎች ግን “ለእነዚህ ሌቦች ዓመት ሙሉ እያጨበጨቡ ኖረዋል” ተብሏል።

የጎፋ ዞን አመራር በኬንቾ የደረሰውን አደጋ ገንዘብ ለልማት ማዋል ሲገባው፣ “እንጨት ከደን ሰብስቦ ፋብሪካ ማቴሪያል ስቶር ወስዶ ቤት ሠርተናል ብሎ ፖለቲካ በመሥራት” ተጠምዷል።

በዞኑ በእርዳታና ድጋፍ የተሠራ አንድም ተቋም የለም። ሁሉም ነገር የተሠራው መንግሥታዊ ባልሆኑ አጋር ድርጅቶችና በፌዴራል የመንግሥት ተቋማት ነው። ለምሳሌ ፌዴራል ፖሊስ 4.5 ሚሊዮን ብር፣ Habitat ደግሞ 88 መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት 46 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ዞኑ ግን እስከ አሁን ያስፈቀደውና የከፈለው ገንዘብ 210 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል። ይህ ሁሉ ገንዘብ እያለ ኬንቾ ሕዝብ ሁሉም ነገር አጥቶ፣ ቤት ያላገኘና የትምህርት ቤት ግንባታ ያልተጀመረለት ተማሪ “ሜዳ ላይ ይማራል”።

ሰሞኑን የተጋለጠውና ለአንድ ግለሰብ የተጻፈው የ60 ሚሊዮን ብር ክፍያ ማዘዣ፣ “እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው” ሲል መረጃው ይኮንናል። የዞኑ መንግሥት ያወጣው ማብራሪያ ደብዳቤውን የፈረሙትንና ትዕዛዙን የሰጡትን ግለሰቦች ለምን እንዳልጠቀሰ ጥያቄ ቀርቧል።

አቶ ጥላሁን ከበደ ያለ ጨረታ ለግለሰቦች ፕሮጀክቶችን በመስጠት፣ አስተዳደርና ፋይናንስን ለሁለት እንዲከፍሉ በማድረግ በርካታ ብልሽቶች እንደፈጠሩ ተገልጿል።

በቅርቡ የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ፋይናንስ አካባቢ ያለውን ችግር ለመቀነስ ቢያቀርብም፣ በጥቅም የሰከረው አስተዳዳሪ ለፋይናንስ መረጃ በመስጠት ፓርቲ ኃላፊውን ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት የመንግሥት ቤት እንዲጠግንና ዕቃ እንዲገዛ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

አቶ ጥላሁን ለራሱ ፍላጎት ሲል ጎፋ ዞንን ለመያዝ፣ አቅም እና ብቃት ያለው አቶ ታምራት ተስማ የተባለውን አመራር ለመከታተል ጭምር የተመደበው በመሆኑ፣ ከክልሉና ከዞኑ አመራሮች ቀጣይ ስጋቶች እየመጡ ነው።

የጎፋ ሕዝብ ተወላጆች እስከመጨረሻው ትግል ለማድረግ መወሰናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ለፌዴራል ገለልተኛ ኦዲተርና ለፌዴራል እንባ ጠባቂ ተቋማት እስከ ቦታው ድረስ በመሄድ የተጎጂዎችን ሁኔታ እንዲያጣሩና የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደገባ ኦዲት በማድረግ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ ጥብቅ ጥያቄ አቅርበዋል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media