በዘይሴ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ‘የዘር ማጥፋት መስፈርት ያሟላል’ ተባለ፤ የጸጥታ አካላት በጤና ጣቢያና ትምህርት ቤቶች ሰፍረዋል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል (ጋሞ ዞን) በሚገኘው በዘይሴ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ኢሰብዓዊ ድርጊት “የዘር ማጥፋት (Genocide) መስፈርትን ያሟላል” ሲሉ የአካባቢው የፖለቲካ ምሁራን ገልጿል።
ኢትዮጵያ በ1948 ዓ.ም. ዓለም አቀፉን የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን ስምምነት ፈራሚ ሀገር ብትሆንም፣ በዘይሴ ሕዝብ ላይ ግድያዎች፣ የንብረት ውድመቶች፣ የአካል ጉዳት ማድረስን ጨምሮ ዘር የማጥፋት መስፈርትን የሚያሟሉ ኢ-ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን ምሁራኑ ለ WT Media ገልጸዋል።
ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ (WT Media) እንደገለጹት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽፋን ሰጭነት፣ የጋሞ ዞን አመራሮች በዘይሴ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የኃይል እርምጃ እየወሰዱ ነው።
በአሁኑ ሰዓት በዘይሴ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ለጸጥታ አካላት ካምፕ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
ለአብነት ያህል፣ የዘይሴ ደንብሌ ጤና ጣቢያ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለኅብረተሰቡ የጤና አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ኃይል (አድማ በታኝ) ካምፕ በማድረግ ተቋሙን እየተጠቀመበት ነው።
ነዋሪዎች ጸጥታ አካላት በዚያ በመኖር “ለሕዝቡ ነፃነትና ሰላም እያሳጡ፣ መንግሥታዊ ሽብርተኝነት እየፈጠሩ” ሲሆን፣ የነዋሪዎችን ቤት ንብረቶችን “በእሳት ወደ አመድነት ሙሉ በሙሉ እየቀየሩ” መሆኑን ገልጸዋል።
በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌዎችና በማዘጋጃ ቤቶች ውስጥም የጸጥታ አካላት ሰፍረው በመገኘታቸው በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ስጋት ነግሷል።
‘የዘመናት ጥያቄን ለማፈን’ የአካባቢው የፖለቲካ ምሁራን፣ የዘይሴ ሕዝብ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ የልዩ ወረዳ የመደራጀት ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ምሁራኑ እንደሚሉት፣ ከጋሞ ዞን አመራሮች መካከል በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የተቀመጡት አካላት ቀደም ሲል የዘይሴን የዘመናት ጥያቄ በስልታዊ መንገድ ሲያፈኑ ቆይተዋል።
አሁን ላይ ግን የዘይሴ ሕዝብ የፖለቲካ መንገዳቸውን ስለነቃ “ሆን ብለው ሙሉ በሙሉ የዘይሴን ሕዝብ ዘር የማጥፋት ዘመቻን” እንደተነሱ ጠቁመዋል።
የዘር ማጥፋት ዘመቻ ፖለቲከኞች ሐሳባቸውን ለማሳካት የሚፈጽሙበት የወንጀል ተግባር መሆኑንም አክለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በጋሞ ዞን ግዞላ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ ታፍነው የታሰሩ የዘይሴ ተወላጆች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ለWT Media ደርሷል። (42 ግለሰቦች ተጠቅሰዋል)
የታሰሩ ግለሰቦች ስም ዝርዝር: መረኩና መታፈራ፣ ወልደ ወዝቦ፣ ኦከ ኡጣይለ፣ አብዩ አብድ፣ ባትረ ባልቻ፣ አየለ ዋይተ፣ መጠጋ አየለ፣ በልጅገ በቀለ፣ አስነጋ አብተው፣ ሙሰ ማላዮ፣ ቀስ መላኩ ከተማ፣ አበል ዳይሾለ፣ አምባዬ ሐሰን፣ አማሞ አምቡላ፣ ድረ ሐሪካሞ፣ ማሜ ገታቸው፣ ጎልና በላቸው፣ ምራፎ ምታቸው፣ ቶማስ ምታቸው።
በተጨማሪም፦ ሙልቀን መለሰ፣ እሸቱ ግሪማ፣ ግዛው ግሪማ፣ አቡሻ ሰበታ፣ ለገሰ ላሌ፣ ገታቸው እጅጉ፣ ማትዮስ ማሪማ፣ ታምራት ሐሰን፣ እንዳለ ጋዳ፣ አስፈራኝ እንዳለ፣ ዮናስ ኩቹፍ፣ አማሬ አድማሱ፣ ይስማው ማትዮስ፣ ደምሉኩ በዛብህ፣ ቁሙላቸው ሞገስ፣ ፖ/ረ ማመድ ስምብሮ፣ ስንቅነሽ ጥላሁን፣ ቦጋለች ቦለ፣ ልብነሽ ጥሩነህ፣ ብዝነሽ ሽቶ፣ ደመቀች ሻሎ፣ ባንች ቦጋለ እና ብሩክታዊት በዛብህ ናቸው።
የዘይሴ ሕዝብ በአስቸኳይ የፌዴራል መንግሥት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጣልቃ በመግባት፣ ሰላማዊውን የዘይሴ ሕዝብ “ከተደቀነው ዘር የማጥፋት ዘመቻ መታደግ አለበት” ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media