ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዎላይታ ሱማሞ ሜዳ ላይ ሊገነባ የታቀደው አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር መክፈል ያለበትን የካሳ ክፊያ መክፈል ባለመፈለጉ ሂደቱ መስተጓጎሉ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ከቦታው ለሚነሱ አርሶአደሮች ለመስጠት የተገመተው የካሳ ክፊያ መጠን በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ቅሬታ በሚያቀርቡ የአከባቢው ነዋሪዎች ላይ የግድያ፣ የእስርና የማስፈራራት ጥቃት እየደረሰባቸው ስለሆነ የፈደራል መንግስት ጠልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።

ከአንድ አመት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በፃፈው ደብዳቤ ድርጅቱ ለመንንባት አቅዶ የቦታ መረጣ በማድረግ፣ በቅርቡ ወደ ስራ ለመግባት በፕላን መሰረት በይዞታ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ማንኛውም ንብረቶች አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ በመፈፀም፣ እንዲሁም ከቦታው ለሚነሱ አርሶ አደሮች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተለዋጭ ቦታ በመስጠት ቦታውን ከይዞታ ነፃ ተደርጎ የይዞታ ማረጋገጫ በአስቸኳይ የሚሰጥበት ሁኔታ እንዲመቻች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሶ ለክልሉ በፃፉት ደብዳቤ ማሳሰባቸውን ይታወሳል።
ሆኖም ግን እንደተባለውም ተቋራጮቹ ክልሉን “በአንድ አመት አጠናቀን እናስረክባለን ቦታውን ከይገባኛል ነፃ አድርጉልኝ” ካሉ አንድ አመት አልፏል፤ በክልሉ እንዲሸፈን የተጠየቀው 130 ሚሊየን ብር ብቻ የካሳ ገንዘብ ቢሆንም ትኩረት ተነፍገው፣ ክልሉ ግንባታ ለማስጀመር መክፈል ያለበትን የካሳ ክፊያ በጊዜው መክፈል ባለመፈለጉ ሂደቱ እንዲስተጓጎል ማድረጉ በአከባቢው ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠረ ስለመሆኑ ተገልጿል።


የግንባታ ሂደቱን ቶሎ ለማስጀመር የፕሮጀክቱ ስራ በሚከናወንበት አከባቢ ንብረትና ቤት ያላቸው አርሶአደሮችን ለማስነሳት ኮሚቴው ተዋቅሮ ስራ ውስጥ የገባ ቢሆንም፣ ሆን ተብሎ በየትኛውም ቦታ ታይቶ የማያውቅ የአርሶአደሩን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ግምት ከ40 ሺህ እስከ 140 ሺህ ብር በሚገመትበት ሁኔታ ላይ ቅሬታ የሚያሰሙትን መግደል፣ ማሰር እንዲሁም ከፍተኛ ማስፈራሪያ እያደረሱ ስለመሆኑ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አርሶአደር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።
ከአራት አመት በፊት ከዎላይታ ሶዶ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ዳሞት ሶሬ ሻምባ ቅለና እና በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋራዛ ቀበሌ ድንበር ላይ እየተገነባ የነበረው አየር ማረፊያ ግንባታ፣ እንዲቋረጥ ተደርገው በአንድ አመት ለማጠናቀቅ የተጀመረው ይሄው አዲሱ የሱማሞ አየር ማረፊያ ግንባታም፣ በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ ክልሉ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር የካሳ ክፊያ ውዝግብ በመፍጠር እንዲሁም ትኩረት በመንፈግ የካሳ ክፊያ በመከልከል፣ እንዲስተጓጎል እያደረገ ስለመሆኑ አንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ምሁር ለሚዲያችን ጠቁመዋል።
የዎላይታ ሶዶ ከተማ ከአስራ ዘጠኝ አምሳዎቹ እስከ አስራ ዘጠኝ ሰባዎቹ ከ20 ዓመታት በላይ መንገደኞችን ሲያስተናግድ የቆየው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎቱን አቋርጠው የነበረ ሲሆን የዎላይታ ህዝብ በፊት የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ በአካባቢው እንዲገነባ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፤ በአስራ ዘጠኝ ዘጠና ዘጠኝ ዓመተ ምህረት የቀደሞው አውሮፕላን ማረፊያ በነበረበት ቦታ ላይ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በመገንባቱ የህዝቡ ጥያቄ ሳይመለስ እንዲቆይ መደረጉንም ምሁሩ ገልጸዋል።
እኚሁ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደማሳያነት ከአንድ አመት በፊት በዎላይታ አረካ አቅራቢያ ለመገንባት በይፋ የተጀመረው የአውሮፕላን ማረፊያ ጉዳይ ሲሆን ተቋራጮቹ ክልሉን “በአንድ አመት አጠናቀን እናስረክባለን ከይገባኛል ነፃ አድርጉልኝ” ካሉ 1 ዓመት አልፏል፤ ከክልሉ እንዲሸፈን የተጠየቀው 130 ሚሊየን ብር ብቻ የካሳ ገንዘብ ቢሆንም ትኩረት በመነፈጉ በአውሮፕላን ማረፊያ እጦት ምክንያት ከተማዋ በርካታ ልማት እያጣች መሆኑም ግልጽ የፓለቲካ ሴራ አካል ነው” በሚልም ገልፀዋል።
ሌላው በዎላይታ ሶዶ ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ የአስፓልት መንገድ ስራ ተስተስጓጉሎ የሚገኝ ሲሆን በቆፈሩበት ቆሟል፤ ምንም እንቅስቃሴ የለም” ሲል አንድ የአከባቢው ነዋሪ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ (WT Media ) አረጋግጧል።
እኚሁ የፓለቲካ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተለው አሁን ያለውን ሁኔታ ከብዙ መነሻዎች በመነሳት ሲገልፅ “እንዲያው ደቡብ ኢትዮጵያ የተባለ ክልል በልዩነት የዎላይታ ህዝብ ጥቅምና ዕድገት ወደኃላ ለመጎተት የተመሠረተ እየመሰለኝ ነው፣ ለምሳሌ በሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና በሕዝብ ብዛት የሚታወቁ አረካና ቦዲቲ ከተሞች ከአለም ባንክ እንዲሰረዙ ተደርጓል። በዚህም በግልፅ የህዝብ ጥቅም የማሳጣት ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ያለ መሆኑን ያስተዋሉት ጥቂቶች ናቸው” ሲል ጥልቅ ትዝብቱን አካፍለዋል።
በተጨማሪም በዎላይታ ሶዶ ከተማ የዞኑ መንግስት ለክልሉ ምስረታ ከሰበሰበው ገንዘብ ከድርሻው 10 ፐርሰንት ባገኘው ገንዘብ ከቀይ መስቀል በዩንቨርስቲ አደርጎ ዴሪ መንደር ይዞ ከገሱባ መንገድ ጋር የሚያገናኝ አምስት ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ግንባታ፣ እንዲሁም ቁስቁም ማሪያም እስከ ዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ጀርባ ይዞ እሰከ ዴሪ ጋንዳባ ድረስ 5 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ 10 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ግንባታ፣ የዎላይታ ዞን መንግስት ከቻይና ሁና ሆንዳ አለምአቀፍ ተቋራጭ ጋር በመነጋገርና በስራ ውል በመስማማት ለማስገንባት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ በመግባት በይፋ ለማስጀመር አቅዶ የነበረ ቢሆንም በክልሉ መንግስት እንዲቆም መደረጉን የፕሮጀክቱን ሂደት ለመከታተል የተዋቀረ ኮሚቴ አባላት መካከል አንድ አባል አስረድተዋል።