በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የረጅም ጊዜ የፖለቲካ ውዝግብ ሲፈጥር የቆየው የብሔረሰብ ማንነት ለውጥ እና የሕዝቦች መጭፍለቅ ጉዳይ፣ “ማዶላ” በተሰኘ በታተመ መጽሐፍ ላይ የተወሰደው እጅግ ከፍተኛ የሕግ ክፍተት ያለበት እርምጃ በመጋለጡ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
WT Media ከተለያዩ ሰነዶች ባገኘው መረጃ መሠረት፣ የአቶ ታደለ ቱፋ “ማዶላ” የተሰኘው መጽሐፍ በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ አመራሮች በሐሰት ክስ መሥርተውበት፣ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 13ኛው ተዘዋዋሪ ችሎት ትዕዛዝ መሠረት 1,200 ቅጂዎች በአርባምንጭ ከተማ በአደባባይ ተቃጥለዋል።


- “ማዶላ” የተሰኘው መጽሐፍ ለምን ተቃጠለ?
የተጋለጠው እውነታ: አቶ ታደለ ቱፋ በ2007 ዓ.ም ባሳተሙት “ማዶላ” መጽሐፋቸው፣ በአሁኑ ወቅት “ጋሞ ዞን” ተብሎ በሚጠራው መዋቅር ውስጥ ያሉ ነባር ሕዝቦች (እንደ ዛይሴ፣ ዶርዜ፣ ቁጫ፣ ግዲቾ፣ ጋንታ፣ ዛርጉላ እና ሌሎችም) ማንነታቸው ተጨፍልቆ እንዲጠሩ መገደዳቸውን በሰፊው ያብራራል።
የአመራሮች ምላሽ: በወቅቱ የነበሩት የፖለቲካ አመራሮች መጽሐፉን “የኛን ማንነት በአደባባይ ያዋርዳል” በሚል በመወንጀል፣ ደራሲውን በሐሰት ክስ መስርተው እስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደርሰዋል።

የፍርድ ቤት ትዕዛዝ: የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 13ኛው ተዘዋዋሪ ችሎት በቀን 19/10/2010 ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ መሠረት፣ 1,200 የሚሆኑት የመጽሐፉ ቅጂዎች በአደባባይ እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ የተሰጠ ሲሆን፣ ትዕዛዙም በቀን 29/ ሰኔ 2010 ዓ.ም. በአርባምንጭ ከተማ መፈጸሙ ተረጋግጧል። ደራሲውም እንዲታሰር ተደርገው ከሁዋላ ህይወቱ አልፈዋል።
- የአካዳሚክ ማረጋገጫ: የፕሮፌሰር ሂሩት ጥናት
ይህንን የደራሲውን ጽሑፍ የሚያጠናክረው፣ እውቅ የዘርፉ ተመራማሪና የቀድሞው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ያካሄዱት ጥናት ነው።
“ገሙ” የሚለው ስያሜ: ፕሮፌሰር ሂሩት እንዳረጋገጡት፣ በዛሬው ጋሞ ዞን በተለይም በደጋማውና በአባያ ሐይቅ አካባቢ ለሚኖሩ በርካታ የተለያዩ ማንነቶች፣ ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክ ለነበራቸው ሕዝቦች (ቁጫ፣ ቦሮዳ፣ ጋንታ፣ ዶርዜ፣ ዘይሴ፣ ካምባ፣ ቦንኬ፣ ኦቾሎ) በአጠቃላይ “ገሙ” የሚል ‘offensive’ (አስነዋሪ) ስያሜ ተሰጥቷቸው ነበር።
የፖለቲካ ስም ለውጥ: ከ1974ቱ የኢትዮጵያ አብዮት በኋላ ግን “ገሙ” የሚለው መጠሪያ ምትክ “Gaamo (Lion)” የሚል ‘synthetic’ (የተፈጠረ) የፖለቲካ መጠሪያ ሥር ላይ መዋሉን የፕሮፌሰሩ አካዳሚክ ጆርናል ላይ ያሳተሙት ጽሑፍ ያረጋግጣል።
- የመጭፍለቅ ውጤት: የትምህርት ችግር
እነዚህ ነባር ብሔረሰቦች ማንነታቸው ተጨፍልቆ እንዲኖሩ ከመገደዱም ባሻገር፣ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር የሚገባቸው ቢሆንም፣ የዚህ የፖለቲካ ውሳኔ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ።

መጽሐፍን በአደባባይ ማቃጠል የዜጎችን የማንነት ጥያቄ በኃይል የማፈን፣ የሕግ የበላይነትን የመጣስና የፖለቲካ ሴራን የመሸፈን አደገኛ ተግባር ሲሆን ይህ የፌዴራል ፍርድ ቤት የሰጠውና የተፈጸመው ትዕዛዝ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የቆዩ የማንነት ጭፍለቃዎችንና የሕዝቦችን ተፈጥሯዊ መብት መገፈፍን የሚያመለክት ታሪካዊ ሰነድ ያደርገዋል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media