1000082179

የዎላይታ ፕሮጀክቶች ለምን የሕዳሴ ግድብ ያህል ዕድሜ ይወስዳሉ? የዝግመቱ ዋና መንስኤዎችና መፍትሔው ምንድናቸው ? ወደ ዎላይታ ግን መሠረት ድንጋይ ይጣላል፣ መሬት ይቆፈራል፣ ወይ ይቆማል ወይም ይታጠፋል! ለምን ?

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዎላይታ ዞን ውስጥ የተጀመሩ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል ፕሮጀክቶች የዓመታት ዕድሜ እያቆጠሩ፣ ከመሠረት ድንጋይ ምሰሶና ከቁፋሮ ያለፈ ውጤት ሳያሳዩ መቆማቸው ለምን? የሚለው ጥያቄ የበርካቶችን አሳስቧል።

WT Media በዚህ ዙሪያ ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ዓለም አቀፍ ምሁር ከሆኑት ፕሮፌሰር ባካሎ አደቶ ጋር ባደረገው ቆይታ፣ የዝግመቱና የመቋረጡን ዋነኛ ምስጢሮች አጋልጠዋል።

1. ዎላይታ እንደ ስጋት እንጂ እንደ ዕድል አይታይም!

ፕሮፌሰር ባካሎ እንደሚገልጹት፣ ዎላይታ ለኢትዮጵያ የሀገር መንግሥት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተችና ከኦሮሞ፣ አማራ እና ትግራይ ቀጥሎ በሕዝብ ብዛት ትልቅ ቦታ የምትይዝ ናት። ይሁንና፣ በለውጡ መንግሥት ትኩረት ከተነፈጉ አካባቢዎች አንዷ ናት፦

የተዛባ አመለካከት:

“ዎላይታን ማልማት ማለት የሀገሪቱን ሁለተኛውን ወይም ሦስተኛውን ደረጃ የሚይዝ አካባቢ ማልማት እንደሆነ የተረዳ ሰው ያለ አይመስለኝም። ብዙ የማዕከላዊ አስተዳደር በትረ ሥልጣን የሚይዙ አገዛዞች ዎላይታን እንደ ዕድል ከመጠቀም ይልቅ እንደ ስጋት የሚያዩበት ሁኔታ አለ።”

የፕሮጀክቶች ዕድሜ:

“በሌሎች አካባቢዎች በሦስትና በአራት ወር ቢበዛ በአንድ ዓመት የሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ወደ ዎላይታ ሲመጡ ግን እንደ ሕዳሴ ግድብ አመታትን ይፈጃሉ። ከሕዳሴ የማይሻለው ነገር ቢኖር ሕዳሴ ስራው ዘገምተኛ እንጂ አንድም አልተቋረጠም። ወደ ዎላይታ ሲመጣ ግን መሠረት ድንጋይ ይጣላል፣ መሬት ይቆፈራል፣ ወይ ይቆማል ወይም ይታጠፋል!”

2. የመዘግየትና የመቆም ምሳሌዎች

ፕሮፌሰር ባካሎ አደቶ ባደረጉት ትንታኔ መሠረት፣ በዎላይታ ዞን ተጀምረው ለዓመታት የቆሙ ወይም የተቋረጡ ዋና ዋና የፌዴራልና የክልል ፕሮጀክቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1. ከሌዊ እስከ ግብርና መንገድ ፕሮጀክት:

በጀት ተመድቦ ጨረታ ከወጣ በኋላ እስከ አራት ዓመት ያህል የፈጀ ሲሆን፣ አሁንም ተንዛዝሎ ቆሟል።

2. ወይቦ ግድብ ፕሮጀክት:

ሥራ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ዕድሜ ብቻ አስቆጥሮ የቆመ ፕሮጀክት ነው።

3. የአየር ማረፊያ ግንባታ:

መጀመሪያ በሶዶ አካባቢ ተጀምሮ ወደ አረካ ሱማሜ ሜዳ የተዛወረ የ9 ወር ፕሮጀክት ቢሆንም፣ አሁን ላይ የቆመበት ሁኔታ አለ።

4. ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል:

ካርታ ተሰርቶ ቦታው ታጥሮ የተቀመጠ ሲሆን፣ ከ10 ዓመት በላይ ቆሟል።

5. ትልቁ የሕክምና ተቋም ግንባታ:

በአፍሪካና በሀገር ደረጃ የሕክምና ዋልታ ይሆናል ተብሎ በ168 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለዎላይታ ሶዶ የተመደበው ተቋም፣ ወደ ሥራ ሳይገባ የውኃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል።

6. የሎጅ ግንባታ ፕሮጀክት:

በዳንኮቴ ግሩፕ በብላቴ አካባቢ ለመገንባት ታቅዶ የነበረው (የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ሎጅ) የት እንደገባ አይታወቅም።

7. የሰመር ሲቲ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች:

በርካታ ተመሳሳይ ከፍተኛ ፕሮጀክቶች ለምርጫ ወቅት ቅስቀሳ ማድመቂያና ድምፅ ማግኛ መሳሪያ ከመሆን ያለፈ ትርጉም ሳይኖራቸው ቆመዋል ወይም አልተተገበሩም።

ፕሮፌሰር ባካሎ፣ እነዚህ ፕሮጀክቶች የሚዘገዩት ለምርጫ ወቅት ቅስቀሳ ከመዋል ባለፈ፣ አካባቢው እንዳያድግ በሚፈልጉና የዎላይታን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦ ጎልቶ እንዳይወጣ በሚፈልጉ የተሰገሰጉ የፖለቲካ ኃይሎች ሴራ ምክንያት መሆኑን አሳስበዋል።

3. የዝግመቱ ዋነኛ መንስኤዎች
ፕሮፌሰሩ እንደ ዋና ችግር ያነሷቸው ሁለት ነጥቦች አሉ።

ሀ. ደካማ የሀገር ውስጥ አመራር

“በአብዛኛው በአካባቢው የሚሾሙ አመራሮች ጠባቂ እንጂ ጠያቂ አይደሉም። የራስን ጥቅምና ምቾት ከማስቀደም ይልቅ ለዎላይታ ህልውና፣ ለዎላይታ ሕዝብና አካባቢ የሚወግን አመራር አለማግኘት ዋነኛ ችግር ነው።”

የዎላይታ አመራር የነቃ ቢሆን ኖሮ በአዲስ አበባ ለሚቸገሩ ሕፃናት ትልቅ ፕሮጀክት ለማስራት ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር መሥራት ይችል እንደነበር፣ እንዲሁም ሆሳዕና ከተማ በስድስት ወር የተሰራውን መንገድ ለጎረቤት ሶዶ ከተማ ለመጠየቅ የቻለ አመራር እንደሌለ ጠቁመዋል።

ለ. የፌዴራልና የክልል የፖለቲካ ሴራ

“ትልቁ ነገር የአካባቢውን የፖለቲካ የበላይነት የያዙ ሰዎች የውሸት ትርክት እየፈጠሩ፣ አካባቢው ከለማና የተቀመጠው ፕሮጀከት ካለቀ አጠቃላይ ለሀገሪቱ ዎላይታ የምታበረክተውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦ ጎልቶ እንዳይወጣ የሚፈልጉ በፌዴራልና በክልል የተሰገሰጉ ኃይሎች መኖራቸው ነው። የፕሮጀክቶች መታጠፍና መዘግየትም ይህን ያሳያል።”

4. የዎላይታ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ

ፕሮፌሰሩ ዎላይታ ለኢትዮጵያ ያለባትን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አፅንኦት ሰጥተዋል፦

ለአብነትም ለሀብትና አቅም:

ዎላይታ በ7 መንገዶች ከተለያዩ አካባቢዎች ጋር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ፣ ከድንጋይ ከሰል ጀምሮ በርካታ ጥሬ ዕቃዎች በቀላሉ የሚገኙባት ናት።

ለሰው ኃይል:

ሕዝቡ ታታሪ፣ ስራ ወዳድና ቀድሞ ዘመናዊ ትምህርት የቀመሰ በመሆኑ፣ በሙያና በፕሮፌሽናል ደረጃ በብቃት መሥራት የሚችል አቅም አለው።

ለለውጡ ድጋፍ:

ሕዝቡ በኢትዮጵያዊ አንድነት የሚያምንና ለሀገር ፍቅር ያለው ሲሆን፣ ለውጡ ሲጀምርና እስካዛሬም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድጋፉን በግልጽ ያሳየ ከመሆኑም በላይ፣ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ያደረገ መሪ ሌላው ደግሞ ቦምብ ጥቃት ሲፈጸም እጁን አክሽፎ የጣለው ዮሴፍ አያሌው የዎላይታ ተወላጅ ነው።

ፕሮፌሰሩ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአካባቢው ትኩረት መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ቢረዱም፣ ይህ በሥራ መረጋገጥ እንዳለበት በማሳሰብ በመጨረሻም በምሳሌ ሆሳና ከተማ በ6 ወር የተሰራው መንገድ ለጎረቤት የዎላይታ ሶዶ ከተማ ለምን የሚል ጠያቂ አመራር የለም እስካሁን በሁለትና በሶስት ማሽን ከተማን አርሰው ማቆየቱ ተገቢነት የለውም ትኩረት ቆሞ ለቀሩ ለዎላይታ አከባቢ ፕሮጀክቶች በሚል አጠቃሏል።