ሰበር ዘገባ: የባለሀብቱ ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ የክስ ድራማ ቀጠለ! የ12 ቢሊዮን ብር ክስ ቢቋረጥም፣ ወዲያውኑ የጋሞ ዞን አዲስ ክስ መክፈቱ ተገለፀ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል – በዎላይታ ተወላጅ ባለሀብቶች ላይ እየደረሰ ነው የተባለው “የግፍ ጽዋ” መልቶ እንደፈሰሰ የሚያመላክተው አዲስ መረጃ ደርሷል።
WT Media ከዚህ ቀደም የዘገበውና በከፍተኛ የፖለቲካ ሴራ የታሰሩት ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ ቢሆንም፣ ወዲያውኑ አዲስ የክስ ድራማ መጀመሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
1. የ12 ቢሊዮን ብር ክስ ተቋረጠ፣ ፍትሕ ግን አልተሰጠም!
ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ በሐሰት ወንጀል ተመስርቶ የቀረበው የ12 ቢሊዮን ብር ክስ፣ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ፋይሉን ዘግቶ ክሱ እንደተቋረጠ ወስኗል።
ባለሀብቱ እስካሁን ድረስ በሳውላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ሲገኙ፣ ከሳሹ አካል (የደቡብ ክልል) “ማስረጃ አላደራጀሁም” እያለ በቀጠሮ ሲያመላልሰው ከርሟል።

በመጨረሻም ክሱ መቋረጡ፣ በእሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ ለዓመታት የደረሰው ስቃይ እና በኢንቨስትመንታቸው ላይ የተደረገው የኪሳራ ሴራ የፖለቲካዊ ጥቃት መሆኑን ያሳያል።
ከዚሁ የግፍ ድርጊት ጋር ተያይዞ፣ የባለሀብቱ ባለቤት ባለቤታቸውን እንዳይጠይቁ ለሶስት ቀናት መከልከላቸው፣ በአንድ ባለሀብት ላይ የሚፈጸመው በደል መጠነ ሰፊ መሆኑን ያጋልጣል።
የሚገርመው እና አስደንጋጩ የሁኔታው ገጽታ፣ ፍርድ ቤቱ የ12 ቢሊዮን ብር ክሱን ውድቅ ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያውኑ የተፈጸመው ነው፦
የግፍ ድራማው ክፍል ሁለት ተብሎ ሊሰየም የሚችለው ይህ ድርጊት፣ በዚሁ ችሎት ዛሬ አዲስ ክስ እንደገና ተከፍቷል።
ለዚህ አዲስ ክስ ቀጠሮ የተሰጠው ለኅዳር 5 ሲሆን፣ ኢንጂነሩ አዲስ ክስ ለመስማት አርባምንጭ እንዲቀርቡ ተወስኗል።
ይህ በባለሀብቱ ላይ የሚደረገው ጥቃት፣ ቀደም ሲል WT Media እንደዘገበው የፌዴራልን የሕግ ሥርዓት ጭምር የሚጥስ ሆኖ ቀጥሏል።
ተከሳሹ ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ለሰበር ሰሚ አቤቱታ አቅርበው፣ አቤቱታውን ለመስማት ሊወስዱት የተላኩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሳውላ ከተማ ሶስት ቀን ከቆዩ በኋላ ተከልክለው መመለሳቸው፣ የክልሉ አመራሮች በጉዳዩ ላይ የፌዴራልን ትዕዛዝ በእምቢተኝነት መከልከላቸውን ያጠናክራል።
በአንድ አልሚ ባለሀብት ላይ የሚደርሰው በዚህ መጠን ያለው በደል፣ “ዎላይታና አካባቢውን ለመስበር፣ አልሚ ባለሀብቶችን መስበር” የተዘረጋ ስልታዊና ስር የሰደደ የፖለቲካ ጥቃት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media