የዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ቦርድ አባላት ክለቡ ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት ከገመገሙ በኋላ በርካታ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል።
በተለይም የ2018 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ የክለቡ አቋም ግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ እርምጃዎች መውሰዱን ማምሻውን ለ WT Media ያደረሰው መሰጃ ያመለክታል።
የክለቡ ቦርድ በሙሉ ድምጽ የሥራ አስኪያጅና ዋና አሰልጣኙን ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ወስኗል።
የቀድሞው ዋና አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ገብረክርስቶስ ብራራ ከክለቡ አሠልጣኝነት ተነስተዋል።
አቶ አሰፋ ሆሲሶ የሥራ አስኪያጅነት ቦታቸውን ለቀዋል።
የክለቡ ሥራ አስኪያጅነት በውክልና አቶ ምትኩ ኃይሌ እንዲመሩ ቦርዱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የክለቡ አሠልጣኝ በመሆን በም/አሰልጣኝ አቶ ተውድሮስ ቀነኒ እንዲመራ ኃላፊነት ተሰጥቷል።

ቦርዱ እንዳብራራው፣ የውጤት ማሽቆልቆል ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፤ በሂደት ለመስተካከል ያልቻሉ ክፍተቶች ነበሩ።
ይህ እርምጃ ክለቡን ለመታደግ እና ሥር የሰደደውን የውጤት ማጣት ችግር ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት በማሰብ የተወሰደ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።
የክለቡ ቦርድ አክለውም፣ በኮቺንግ ስታፍ ውስጥ መፈተሽ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸው፣ ተከታታይ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም፣ የክለቡ ቦርድ መላውን ደጋፊዎችና የስፖርት አፍቃሪያን በስፖርት ጨዋነት ክለባቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።