በመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች ዘንድ በፆም፣ በፀሎት እና ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊትን በመኮነን በታላቅ ድምቀት በየአመቱ የሚከበረው የኢድ አል አድሀ/ አረፋ በዓል መላው የተቋሙ ተማሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
ወንድማማችነት እና የአብሮነት እሴትን መሰረት ባደረገ መልኩ ያለምንም የሀይማኖት ልዩነት በዩኒቨርሲቲው በተከበረው በዚህ ሐይማኖታዊ በዓል በተማሪዎች ዘንድ “አባታችን” በመባል የሚታወቁት ፕ/ር ታከለ ታደሰ፣ የአካዳሚክ ጉዳዬች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ዴአ፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መስፍን ቢቢሶ፣ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር መ/ር ተመስገን ማርቆስ እና ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የኢድ አል አድሀ-አረፋ በዓል በታላቅ ድምቀት ሊከበር ችሏል።
የኢድ አል አድሀ-አረፋ በዓል የእምነቱ ተከታዬች አንድነታቸውንና አብሮነታቸውን አጠናክረው በላቀ ወንድማማችነት እርስ በርስ የሚረዳዱበት፣ የሚተሳሰቡበት እናም የሚደጋገፉበት ታላቅ በዓል መሆኑን በበዓሉ የተገኙት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ገልጸው፤ ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የእስልምና ህግጋት እንደሚፈቅዱት የመታዘዝ እሴቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሊሆን እንደሚገባ አውስተዋል።
የኢድ አል አድሀ/ አረፋ በዓል የደግነት፣ የቸርነት ብሎም ያለንን የማጋራት በዓል መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የእምነቱ ተከታዬች በዓሉን ከተቸገረው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በጋራ ማክበር ተገቢ እንደሆነም ተናግረል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የብልጽግና፣ የከፍታ፣ የአብሮነትና የአንድነት እንዲሆን ጭምር ፕ/ር ታከለ ታደሰ መልካም ምኞታቸውን ገልጿል ሲል የዩኒቨርስቲው ኮሙኒኬሽን ዳይረክተር ዘግቧል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 13/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
