GridArt_20251112_144825917

TopUrgent #BreakingNews

በጅንካ ጀነራል ሆስፒታል ያልታወቀና ከፍተኛ ሞት የሚያስከትል በሽታ ተከስቶ ዶክተሮችን ጨምሮ ሌሎች አምስት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ማድረጉ ተነገረ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ ጀነራል ሆስፒታል አካባቢ ምንነቱ ባልታወቀና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት በሚዳርግ በሽታ የተያዙ ሰዎችን ተከትሎ በከተማው ከፍተኛ ሥጋት መከሰቱ ተገልጿል።

WT Media ከሆስፒታሉ የደረሰው የውስጥ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ እስካሁን በበሽታው ምክንያት 5 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ በተጨማሪም ትላንትና ምሽት ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ሞተዋል፣ ከእነዚህም አንዱ የሆስፒታሉ ነርስ ነው።

የሆስፒታሉ ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ በሽታው በአጭር ጊዜ ውስጥ ማለትም በ3 እስከ 5 ቀናት ውስጥ ለሞት እየዳረገ ነው።

የበሽታው ምልክቶች: መጀመሪያ ላይ ከትኩሳት (AFI) ጋር ተመሳሳይ ምልክቶችን ያሳያል፤ ከዚያም ወደ ከፍተኛ ደም መፍሰስ (bleeding) እና የብዙ የሰውነት አካላት መሥራት አለመቻል (multiorgan failure) ይቀየራል ተብሏል።

የሕክምና ምላሽ እጥረት: በሽታው እንደ Arthisunate፣ Ceftriaxone፣ Vancomycine እና ሌሎችም ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች በሚሰጡ መድኃኒቶች ምንም ዓይነት ምላሽ አለመስጠቱ የችግሩን አሳሳቢነት ያሳያል።

የንክኪ ስርጭት ሥጋት: የሞቱት ሰዎች በሙሉ መጀመሪያ ላይ ከሞተው ታማሚ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ የነበራቸው መሆኑ እና በሁሉም ላይ ተመሳሳይ ምልክቶች መታየታቸው በሽታው የመተላለፍ አቅም ያለው መሆኑን ያመለክታል።

በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እና የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ራሳቸው ለሞት መዳረጋቸው በጅንካ ሆስፒታል ከፍተኛ ፍርሃት ፈጥሯል።

ባለፈው ሳምንት በሽተኛውን ሲያክም የነበረ አንድ ዶክተር ትላንት በስቲያ ሰኞ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ምሽት ላይም አንድ ነርስ በዚሁ ምክንያት መሞቱ የጤና ባለሙያዎችን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ጥሏል።

በጅንካ ሪፈራል ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አዛዥ ዳቲኮ በሰጡት አስተያየት፣ ሁኔታውን “በጅንካ ከፍተኛ ሞት ያለው (100%) ያልተገለጸ በሽታ” በማለት ጠርተውታል።

“ውጤቱ ለሕዝብ እስኪገለጥ ድረስ እንደ ኮቪድ እራሳችሁን ጠብቁ! … ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ጠንካራ እና አፋጣኝ የሆነ አገር አቀፍ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ያስፈልጋል” ብለዋል።

በከተማዋ የተለያዩ ወሬዎች እየተናፈሱ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞች የክልሉ ጤና ቢሮ እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስለ ሁኔታው አስፈላጊውን መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ እና ለባለሙያዎችም ሆነ ለሕዝቡ ተገቢውን የጥንቃቄ መመሪያ እንዲሰጡ አጥብቀው ጠይቀዋል።

ከክልሉ ጤና ቢሮ WT Media ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media