በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ለተከሰተውና በ3-5 ቀናት ውስጥ ሰዎችን ለሞት እየዳረገ ላለው ምንነቱ ለጊዜው ያልታወቀ በሽታ፣ የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አፋጣኝ ይፋዊ መግለጫ መስጠቱን WT Media አረጋግጧል።

ይህ መግለጫ የመጣው የሆስፒታሉ ሠራተኞችና ነዋሪዎች የክልሉ መንግሥት ትኩረት ባለመስጠቱ ከፍተኛ ቅሬታቸውንና ሥጋታቸውን ለ WT Media ከገለጹ ከሰዓታት በኋላ ነው።
የሆስፒታሉ ሠራተኞች፣ የክልሉ ጤና ቢሮ የጥንቃቄ መልዕክቶችን አለመስጠቱና ሕዝቡን አለማረጋጋቱ “ለበሽታው ዕድል እንደመስጠት” እንደሆነ ቅሬታቸውን ገልጸው ነበር።
ተኝተው የሚታከሙ ህሙማንና ወላድ እናቶች ያሉባቸው ክፍሎች ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን የሕክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ ውስጥ ያለው የህክምና ቁሳቁስ እጥረት ዋነኛ ሥጋት ሆኖ ቀጥሏል።
በሽታው መጀመሪያ ላይ ከትኩሳት (AFI) ጋር ተያይዞ፣ በፍጥነት ወደ ከፍተኛ ደም መፍሰስ እና የብዙ አካላት መሥራት አለመቻል ምልክቶች እየተለወጠ ነው።
የሆስፒታሉ ሠራተኞች የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት፣ የጤና ሚኒስቴር በጅንካ የተከሰተውን ሁኔታ አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ በመስጠቱ WT Media ምስጋናውን አቅርቧል። መግለጫው ወዲያውኑ ወደ ተግባር መግባትን የሚያመለክት ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች እስካሁን ምንም መግለጫ አለመስጠታቸው ቀጥሏል። ከጤና ሚኒስትር መግለጫ ውጪ እስካሁን የትኛውም የመንግሥት ሆነ የግል ሚዲያዎች ለዘገባው ሽፋን አልሰጡም።
WT Media የጤና ሚኒስቴርን መግለጫ ይዘትና የፌዴራል መንግሥት የሚወስዳቸውን አፋጣኝ እርምጃዎች ተከታትሎ ለሕዝብ የሚያደርስ መሆኑን ያስታውቃል።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media
1 thought on “የWT Media ዘገባ ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር በጅንካ አደገኛ ወረርሽኝ ዙሪያ ይፋዊ መግለጫ ሰጠ!”
Comments are closed.