GridArt_20251113_162753657

በጅንካ አደገኛ ወረርሽኝ ዙሪያ የዓለም ጤና ድርጅት መግለጫ በማውጣት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ መድቦ ባለሙያዎችንና የሕክምና ቁሳቁሶችን ወደ ጅንካና አከባቢው መላኩን አስታውቋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አካባቢ በ3-5 ቀናት ውስጥ ሰዎችን ለሞት እየዳረገ ባለው ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ዙሪያ፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ምላሽ ለመስጠት ወደ ተግባር መግባቱን በይፋ አስታወቀ።

WT Media ያቀረበው የቅሬታ ዘገባ ተከትሎ ይህ የዓለም አቀፉ ድርጅት አፋጣኝ ምላሽ የመጣው፣ WT Media በትላንትናው ዕለት በሆስፒታሉ ሠራተኞችና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያለውን ከፍተኛ ሥጋት መሠረት በማድረግ ባቀረበው ተከታታይ ዘገባዎች ማግስት ነው።

WHO ይህን ወረርሽኝ “የቫይራል ደም መፍሰስ ትኩሳት (Viral #Haemorrhagic Fever – #VHF) ሥጋት” እንደሆነ ገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ፣ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልላዊ የጤና ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

እስካሁን 8 ሰዎች፣ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ፣ በበሽታው መያዛቸው እንደተዘገበ ተጠቅሷል።

WHO ባለሙያዎችን፣ መድኃኒቶችን፣ የሕክምና ቁሳቁሶችን እና ለጤና ሠራተኞች የሚሆኑ የግል መከላከያ መሣሪያዎችን (PPE) ወደ ጅንካና አካባቢው ልኳል።

የዓለም ጤና ድርጅት ለምርመራ የሚሆኑ ናሙናዎችን መላኩንና ተጨማሪ ዝርዝሮች በቅርቡ እንደሚጠበቁ አስታውቋል።

ሊከሰት የሚችለውን ድንበር ተሻጋሪ ስርጭት ለመከላከል በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የWHO ቅርንጫፎች በቅርበት እየተባበሩ ነው።

አስቸኳይ ድጋፍ ለመስጠት 300,000 የአሜሪካን ዶላር ከ WHO የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ መከላከል ፈንድ (Contingency Fund for Emergencies) መለቀቁ ተገልጿል።

ዳይሬክተሩ የኢትዮጵያ የጤና ባለሥልጣናት መረጃን በጊዜያዊነት በማካፈላቸው እና ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው አድንቀዋል።

በሽታው በ3-5 ቀናት ውስጥ ለሞት የሚዳርግ፣ ከትኩሳት ወደ ደም መፍሰስና የብዙ አካላት መሥራት አለመቻል የሚቀየር አደገኛ ባሕሪ እንዳለው፣

የክልሉ ጤና ቢሮ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ባለመስጠቱ እና የሆስፒታሉ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ ከፍተኛ ቅሬታ ገልጸው ለፌዴራሉ መንግሥት ጥሪ አቅርበው ነበር።

የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ትናንት ይፋዊ መግለጫ መስጠቱ ተከትሎ፣ የዓለም ጤና ድርጅትም በዛሬው ዕለት ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ግን እስካሁን ምንም ዓይነት ይፋዊ መግለጫ አለመስጠታቸው ቀጥሏል።

WT Media ሁኔታውን እና የሚወሰዱትን እርምጃዎች ተከታትሎ ለሕዝብ ያደርሳል።

ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media