የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በመጪው ቅዳሜ በይፋ ወደ ስራ የሚገባበትን የማብሰሪያ ፕሮግራም ለማካሄድ ያቀደውን ቦታ ቀይሮ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ አደረገ።

ሚዲያው ቅዳሜ በቀን 17/11/13 ዓ.ም በዎላይታ ሶዶ ከተማ ያዕቆብ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከረፋዱ 4:30 ጀምሮ ለማካሄድ ቀደም ብሎ መግለፁን ተከትሎ በማብሰሪያ (Launching) ፕሮግራሙ ላይ ለመገኘት በርካታ ሰዎች ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ እንዲሁም በሆቴሉ ተደራራቢ ፕሮግም በዕለት በመኖሩ ከዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር ባደረግነው መግባባትና ትብብር በትልቁ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ ላይ ለማካሄድ በፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ተወስኗል።

በኘሮግራሙ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ወጣቶች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ የንግዱ ዘርፍ ግለሰቦች፣ ጋዜጠኞች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች የሚገኙ ሲሆን እርሶም የሚዲያው አጠቃላይ የስራ ሁኔታ በሚቀርብበት እንዲሁም የፕሮግራሙ ታዳሚዮች በሚዲያው ቀጣይ ስራ ላይ አስተያየትና ሀሳብ በሚሰጡበት መድረክ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

በኢትዮጵያ በተለይ በክልሉም ሆነ በዞኑ የመጀመሪያው የበይነመረብ መገናኛ ሚዲያ አማራጭ የሆነው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፣ ከኢትዮጵያ መገነኛ ብዙሃን ባለስልጣን ህጋዊ ፈቃድ በማግኘት በይፋ ስራውን ለመጀመር የማብሰሪያ ፕሮግራም በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትልቁ የተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ ቅዳሜ በቀን 17 /11/13 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ጀምሮ በሚያካሂድበት እንዲገኙ በድጋሚ በክብር ስንጋብዞት በታላቅ ደስታ ነው።

በመድረኩ እንዲገኙ ለተለያዩ አካላት የጥሪ ግብዣ ካርድና የቦታ ቅያሬ በፕሮግራሙ አስተባባሪዎች አማካይነት እየደረሰ መሆኑን እየገለፅን በተለያዩ ምክንያት የግብዣ ካርድ ያልደረሳችሁ በውስጥ መስመር መልዕክት ብታስቀምጡ በአስተባባሪዎች አማካኝነት እንደሚደርሳችሁ እንገልፃለን።

በዚህ ታሪካዊ ቀን በመገኘቶዎ እናመሰግናለን🙏

ሚዲያ የልማት አንቀሳቃሽ ሞተር ነው🙏

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡWolaita Timesese/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1 በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times , 13/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹