በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ አሳሳቢ የጸጥታ ችግር ባለበት እና የዘይሴ ሕዝብ “የተደራጀ የዘር ማጥፋት ዘመቻ” እየተካሄደብን ነው በሚል ወደ ጫካ እንደገባ በሚዘገብበት ወቅት፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በአርባምንጭ እየተካሄደ ባለው “ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ” ላይ የሰላም አምባሳደር ተብለው መሸለማቸው የሕዝብን ቁጭት ቀስቅሷል።
WT Media ከስፍራው ባገኘው መረጃ መሠረት፣ ይህ የሰላም ኮንፈረንስ የተጀመረው በዘይሴ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን “ግፍ፣ ግድያ፣ እስርና ንብረት ውድመት” ለመሸፈን በተደረገ ስልታዊ እንቅስቃሴ ነው።


የዘይሴ ብሔረሰብ አባላት ለ WT Media በላኩት ተማጽኖ፣ ከሀገር አቀፍ ደረጃ የመጡ የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች “በደላችንን እንዲሰሙ” ጥሪ አቅርበዋል።
ወጣቶቹ የሰላም ኮንፈረንሱ እየተካሄደ ካለበት አርባምንጭ ከተማ “በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለው የዘይሴ ሕዝብ ስቃይ ውስጥ ነው” ብለዋል። “የተደራጀ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደቀጠለ” ተሳታፊዎቹ እንዲያውቁ መልዕክት ልከዋል።
የዘይሴ ሕዝብ በሕገመንግሥቱ የተደነገገውን የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በመጠየቁ ብቻ፣ “በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች፣ አዛውንቶችና ሴቶች እየተገደሉ፣ ቤት እየተሰበረና የተመረተው ምርት (ሙዝ፣ በቆሎ) በእሳት እየተቃጠለ” እንደሆነ WT Media በተደጋጋሚ ዘግቧል።
በአንድ በኩል ዘይሴዎች “በአቶ ጥላሁን ከበደ አሸባሪው ቡድን” ግድያ እየደረሰብን ነው ብለው ወደ ጫካ መግባታቸውን ሲገልጹ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ጥላሁን ከበደ በዚሁ ክልል “የሰላም አምባሳደር” ተብለው መሸለማቸው፣ በክልሉ እየተፈጠረ ያለውን የእውነትና የውሸት ትርክት ልዩነት በግልጽ ያሳያል።
የዘይሴ ወጣቶች አቶ ጥላሁን ከበደ “የሰላም ተምሳሌት” በማለት እለት እለት የሚሰብኩት “የውሸት ስብከት” መሆኑን በመግለጽ፣ የፌዴራል መንግሥት በቦታው ወርዶ እውነቱን እንዲያጣራ ተማጽነዋል።
WT Media ቀደም ባለው ዘገባው የፌዴራል መንግሥት ለዚህ ጭካኔ የተሞላበት ዘር ማጥፋት ዘመቻ ትኩረት አለመስጠቱ አሳሳቢ መሆኑን በመጥቀስ፣ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሕዝቡን ቀርበው ማናገር አለመፈለጋቸው” ሕዝቡን የበለጠ እንዳስቆጣው ዘግቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዘይሴ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ በፎቶና በቪዲዮ ተደግፎ ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤትና ለሰብዓዊ መብቶች ተቋማት ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ይታወቃል።
ማሳሰቢያ፦ WT MEDIA በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media
R