IMG_20251114_155025_141

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ስር የሰደደ የሙስና እና የሀብት ምዝበራ ላይ ትኩረት የሚያደርግ በተለይም በከፍተኛ አመራሮች በተጠረጠረበት የጎፋ እርዳታ ገንዘብ ምዝበራና የግብር ስርቆት አስቸኳይ የኦዲት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።

የክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ኦዲተሮች ወደ ጎፋ ዞን መላኩን WT Media ከተአማኒ ምንጮች አረጋግጧል።

ኦዲተሮቹ በተለይም በሁለት ዋና ዋና የሙስና መገለጫዎች ላይ ጥብቅ ማጣራት እንዲያደርጉ ተልከዋል፦

በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጊዜ ከአለምአቀፍ ድርጅቶች፣ ከበጎ አድራጎት ተቋማት እና ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰበሰበው የእርዳታ ገንዘብና ዕቃዎች ምዝበራ ላይ ማጣራት ይደረጋል።

ገንዘቡ በሕጋዊ መንገድ አስመስሎ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እንዲሁም የተለያዩ የክልል እና የዞን አመራሮች በመሆን የሕክምና ቁሳቁስ፣ የምግብ ዘይት፣ አልባሳት እና የግንባታ ዕቃዎችን እስከ ዛሬ ድረስ እያሸሹ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በጎፋ ዞን የገቢዎች ጽ/ቤት የመንግሥት ገቢ መሰብሰብ ትቶ፣ ግብርን በሕገወጥ ደረሰኝ በመሰብሰብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ የክልል እና የዞን የአመራሮች ዘመድ አዝማድ የሆኑ የገቢዎች ባለሙያዎች ላይ ጠንካራ ማጣራት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ለአብነት በአንድ የገቢ ሠራተኛ ላይ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የኦዲት ግኝት እንዳለበት እና ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ገቢ የቀጠፉ ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡ ይደረጋል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ኦዲት ለማድረግ የሄዱ ገለልተኛ ኦዲተሮች እንዳስረዱት፣ ይህ መረጃ እንዳይወጣ የክልሉ አመራሮች ብርቱ ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ፣ ኦዲተሮቹ በዛሬው ዕለት ወደ ስፍራው በመድረስ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፦ #WTMedia በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።

ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media