እባካችሁን ይብቃችሁ እኛም ታክቶናል!
/ነፃ ሀሳብ/ / ከ WT Media – በዳርጋሶ ዳጬ ከዎላይታ ሶዶ
ርቱዕ ፍትህ ከሰፈነ ህዝብ የሚያነሳቸዉን የልማትም ሆነ ሌሎች በርካታ ጥያቄዎቹን ታግሶ ያልፋል፡፡ መንግስት በሂደት ድምፀቱን እንደሚሰማ አምኖና ተቀብሎ ያዘግማል፡፡
አንድ ማህበረሰብ በፍትህ ሚዛን በእኩል አለመታየት እና የተዛባ እንዲሁም ሆን ተብሎ የሚደረግን ሸፍጥ ግን በምንም ስሌት አይታገስም፡፡ ለጊዜዉ ቢያዳፍን እና ቢዳፈንም ቅሉ ረመጡ ዉስጥ ለዉስጥ ተብላልቶ ተጋግሞ ይንቦለቦላል፡፡ ዎላይታ ላይ እየሆነ ያለዉም ይኸዉ ነዉ፡፡
በሁሉም ዘዉግም ሆነ ዘርፍ ታላቅ የሆነን ህዝብ ለማሳነስ፤ ደማቁንና ግዙፉን ታሪኩን ለማኮሰስ፤ ተዝቆ የማያልቀዉን ባህሉን ለማራከስ፤ ጀግንነቱን ለመካድ ታሪኩን ለማጠልሸት እንዲሁም ማንነቱን ለማመሰቃቀል በትናንሽ ካድሬዎች እና ሆድ አደሮች እዚህም እዚያም የሚረጩ መርዞች ከወዲሁ ካልከሰሙ መዘዛቸዉ ዛሬ እንደቀልድ እንደምንሰማዉ ነገ ቀለዉ አናገኛቸዉም፡፡
መሰረታዊዉ የዎላይታ ህዝብ አለታማ ዉቅሩ የመደብ ችግር የለበትም፡፡ ከትዉልድ ቄየዉ እስከ ባዕድ አገር በስደት የሚኖረዉን ዎላይታ ብታነጋግሩ ከዎላይታነቱ ዝቅ ብሎ መንደር ለመንደር አይርመጠመጥም፡፡ ታሪኩን ጠንቅቆ የሚያዉቅ፤ የአባቶቹን ታሪክ በኩራት የሚተርክ፤የእርሱንም ድርሻ በስራ ሊከትብ ስራ ሳይንቅ ጥሮ ግሮ ለፍቶ የሚያድር ታታሪ ህዝብ ነዉ፡፡
ይህን ስንል በህዝብ ስም ለስልጣንና ለግል ጥቅም የሚራኮት ቡድን የለም ብዬ በጭፍን የምጋልብም አይደለሁም፡፡ በክላስተር ተደራጅቶ፤ በቤተ እምነት ተቧድኖ ሊሰርቅ በደረቱ የሚሳብ ከክልል እስከ ወረዳ መዋቅር ድረስ ሞልቷል፡፡ ይህም ቢሆን ግን በአንድ እጁ ጥቅሙን በሌላዉ እጁ ደግሞ ማንነቱን አቻችሎ ለመሄድ ሲታትር ይስተዋላል፡፡
ይህ ድርጊታቸዉ ደግሞ ገና ከጅምሩ በአዲሱ ክልል ዎላይታ የሚገባዉን ተነፍጎ የበዪ ተመልካች፤ የደጋሾች ቀላዋጭ እና የመሪ ተዋናዮች አጨባጫቢ እንዲሆን አስገድዶታል፡፡
እነ ጋሽ ፍሬዉ አልታየን የወለደ የዎላይታ ምድር “እንዴት የክልል ፕረዝዳንትን በደብዳቤ እጠይቃለሁ” የሚል ዞን አስተዳዳሪ አድርጎ አሳየን፡፡ ዳጋቶን የወለደችልንን የዎላይታን እናት አመስግነን ሳናበቃ ቀጥለው የህዝብ ጥቅም አሳልፈው የሰጡትንም ዎላይታ ናቸው ተባልን፡፡
በየደረጃዉ ክልል ላይ ያሉትም በጣት ከሚቆጠሩት ዉጪ ሀርድ ቶፕ መኪናቸዉ የነዳጅ ኪሳቸዉን ከርሳቸዉ የቁርጥ ገንዘብ አይጉደል እንጂ ስለ ዎላይታ ምድርና ስለ ዎላይታ ህዝብ የሚገደዉ ጥቂቱ ነዉ፡፡

ከዎላይታ ሶዶ 3 እና 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የጎርፍ ዉሃ የሚናፍቀዉ ህዝብ አለን፡፡ የሚሸት የኩሬ ዉሃ ብርቁ የሆነበት፤ አሸዋ ምሶ ደለል ቆፍሮ በጨርቅ አጥልሎ የሚጠጣም ህዝብ ብዙ አለን፡፡ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ላይ በሽር ወንዝን ሌሊት ተነስቶ ቀድቶ የሚጠጣ ዜጋ አለን፡፡
ቦርጫቸዉን ያንጠለጠሉ የህዝብ ተመራጮቻችን ይህንን አያዩም፡፡ በየመምሪያዉ የተሰገሰጉ የዎላይታ ካቢኔዎች ያልተሰራ የዉሸት ሪፖርት ከሽነዉ ከማቅረብና ወንበራቸዉ እንዳይነቃነቅ ትርፍራፊ ለቃቃሚዎችን በዙሪያቸዉ ኮልኩለዉ እከሌ ስለ እኔ ምን ፃፈ ከሚል ዝቃጭ አስተሳሰባቸዉና ፍራቻቸዉ ተላቀዉ ለህዝባችን ጠብ የሚል ነገር አይሰሩም፡፡ከየመምሪያዎቹ አበል አንዳቸዉ ለአንዳቸዉ እየተፃፃፉ ይዝረፉ እንጂ፡፡
የዞኑ አስተዳዳሪ አማካሪ ተብየዎችም በመቁረቢያ ዕድሜያቸዉ እከሌ ይወድሃል እከሌ ባንተ ስልጣን ይቀናል እያሉ ነገር እያቀሳሰረሩ ከመብላት የዘለለ እንኳን ሊያማክሩ ሲመከሩም የሚገባቸዉ አይደሉም፡፡
የዛሬይቱ ዎላይታ የፎቶ ፖሊቲካ እየናጣት ነዉ፡፡የሚፖሰት ፎቶ ቁጥርና ጥራት እንጂ መሬት ላይ ያለዉ ስራ ባለቤት አልባ ነዉ፡፡
የሰሞኑን ጉድ ልንገራችሁ፡፡ አቶ ገብረመስቀልና ሌሎችም ቱባ የዎላይታ ባለስልጣናት የዳጋቶን አባት ለቅሶ ለመድረስ ወደ ዳሞት ፑላሳ ሻንቶ ሄደዉ ሲመለሱ ከዎላይታ ሶዶ ቦዲቲ መግቢያ አካባቢ አንዲት የበሬ ግንባር የምታክል ማሳ ላይ አንድ አርሶ አደር ከመንግስት የተደረገለት አንዳች ድጋፍ ሳይኖር በራሱ ጥረት ማዳበሪያ እንኳን ከገበያ በዉድ ዋጋ ገዝቶ የዘራዉን የስንዴ ማሳ ረጋግጠዉ ወጥተዉ “በዘንድሮ የምር ዘመን የተሻለ የስንዴ ምርት” እያሉ ሲቀደዱ ምንም አያፍሩም፡፡ ከማሳዉ እኮ 10 ኩንታል እንኳን አይገኝም፡፡
ይህ ስብዕናቸዉ ነዉ ዛሬ ላይ ዎላይታን ዝቅ አድርገዉ ሌሎቹ ይፈነጩ ዘንድ በር የከፈተዉ፡፡ ሁሉም የጥላሁንን መፀዳጃ ገላ ለመላስ የመራኮታቸዉ እርሾ ማንነታቸዉን እና መነሻቸዉን አለማወቃቸዉ ነዉ፡፡ በአዲሱ ክልል ዎላይታ የመሪነት እንጂ የአጨባጫቢነት ድርሻን ይዞ እንደማየት ዉርደት የለም፡፡
ጥላሁን ያሰማራቸዉና የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት ተብለዉ ተከፋይ ወጠጤዎች በማህበራዊ ሚዲያ ዎላይታን በማንነቱ ሲሰድቡ፤ ጸያፍ ቃላትን ተጠቅመዉ ታልቅ ስሙን ሲያጎድፉ ለምን የሚል ጠፍቶ ቂጡን ያልጠረገ ሁላ ሲሳደብ የዎላይታ ተወካይ ነን ባዮች ጨርቅ ለብሰዉ ያለ “ሰዉነት” ህዝብ መሃል ይመላለሳሉ፡፡
ዎላይታ አሸርጋጅ አያዉቅም ነበር፡፡ አሁን ግን ሁሉም አመራር ሽንታም እየሆነብን ተቸገርን፡፡በድብቅ እንጂ በገሃድ እዉነትንና አመክንዮን አሰናስሎ ለምን የሚል ተኮላሽቶ ከስሟል፡፡ በየግሮሰሪዉ ተከሽኖዉን እየተጋተ ሀሜት እንጂ ህዝብን በመረጃ አጎልብቶ ህብረትን ሰብኮ የሚሟገት የለም፡፡
በቅርቡ በአስቸኳይ የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ጥላሁን ከክልሉ ህዝብ ጫንቃ ላይ ይገነደሳል፡፡ ገብረመስቀልም እርጅናዉ ተጫጭኖታል መሰለኝ ስለ ጡረታ እያወራ ነዉ፡፡ እርሱም ይሸኛል፡፡ ማንም ሄደ ማንም መጣ ዎላይታ ስለ ማንነቱ በብርቱ ሊሞግት ይገባል፡፡ መብቱንና የሚገባዉን ሊጠይቅ ለሌሎችም መከታ ሊሆን የተፈጠረ ታላቅ ህዝብነቱን ዳግም ማስመስከር አለበት፡፡ በጥላሁን ይሁንታ የሚለማ በጥላሁን ንፍገት የሚከፋ ህዝብ የለንምና እባካችሁን ከዚህ በላይ አታስደፍሩን፡፡
እባካችሁን ይብቃችሁ እኛም ታክቶናል!
/ነፃ ሀሳብ/ / በ WT Media የተዘጋጀ
በዳርጋሶ ዳጬ ከዎላይታ ሶዶ
ማሳሰቢያ፦ #WTMedia በሀገሪቱ በተለይም ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት በማያገኙ ለተጮቆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥተው እውነትንና ሀቅን መሠረት አድርገው የሚሰራ ስለሆነ የመረጃ ሰጪ ግለሰቦች ምስጥርና ደህንነት በተጠበቀ ሁኔታ የደረሱን መረጃዎችን መልሰን አጣርተን ለህዝብና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት በታማኝነት ይፋ እናደርጋለን።
ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ፋይዳ ባላቸው ህዝብ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን ለማካፈል ለሚፈልጉ ሁሉ ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነን እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚፀባረቅበት በሌሎች ትላልቅ ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለ ዘውትር አብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!! እኛ ዘውትር የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን !!
Voice of Marginalized Community – WT Media