ሰበር ዜና: የአለም ትኩረት ስለሆነው በሽታ የተናገረው የጅንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ከሥራ ታገዱ!
በጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ለተከሰተውና መርበርግ ( #Marburg ) ተብሎ ለተጠረጠረው አደገኛ ቫይረስ ወረርሽኝ መረጃ በመስጠት ዙሪያ ውዝግብ ተነስቷል።
WT Media ከውስጥ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሠረት፣ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቢኒያም አስራት ከኃላፊነታቸው ታግደዋል።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ከሥራ መታገዳቸው የተዘገበው መርበርግ የተባለ አደገኛ ቫይረስ የ6 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል ተብሎ በተገለጸ ማግስት በመሆኑ በአካባቢው አነጋጋሪ ሆኗል።

ለWT Media መረጃ የሰጡ የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት፣ ሜዲካል ዳይሬክተሩ የተባረሩበት ምክንያት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በቫይረሱ የሞቱ ዜጎች መኖራቸውን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የዶክተሩ ከሀላፊነት መባረሩ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን ለትላልቅ አለም አቀፍ ሚዲያዎች መረጃ ሰጥተው የገጽታ ግንባታ አበላሽቷል በሚል ክስ እንደሆነም በምንጮቹ ተረጋግጧል።

አንድ የክልሉ የጤና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያ ተጠይቀው እንደገለፁት “ከጤና ሚኒስቴር በኩል እንጂ ምንም አይነት መረጃና መግለጫ የክልሉ መንግስት የመስጠትም ሀላፊነት እንደሌለ በመግለፅ የተኛውም የመንግስት ሚዲያዎችም በጉዳዩ በተለይም ከበሽታ ጋር ተያይዘው ህይወት ያለፋቸው አካላት ተጠቅሶ እንዳይዘገብ የሚለው አቋም ተይዟል” ብሏል።
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ጥረት እያደረግን ነው።
የተፈጠረው የቫይረሱን ክስተት አስመልክቶ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ቀድሞ WT Media በተደጋጋሚ ባቀረበው ዘገባ ተከትሎ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እና የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መግለጫ እንዲሰጡ እና በሽታውን ለመከላከል በትኩረት ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉ ይታወሳል።