GridArt_20251118_163758121

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ34 ዓመት ወጣት ባለሀብት ላይ “የ12 ቢሊዮን ብር ክስ ከሽፎ፣ “የዜይሴ ህዝብ ያስታጥቃል” ክስ መሠረት ቢስ በመሆን ተከትሎ “ለፖሊስ የቤት ቆጣሪ አስገብታሃል” የሚል አዲስ አስቂኝ ክስ መጀመሩ ተገልጿል።

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፦ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የፖለቲካ ሴራ ሰለባ ሆኗል እየተባለ በሚዘገበው ወጣት ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ ቀደም ሲል የተመሰረተው የ12 ቢሊዮን ብር የኪሳራ ክስ በፍርድቤት ውድቅ መደረጉን ተከትሎ፣ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ሌላ አዲስ የወንጀል ክስ መክፈቱን የሚያረጋግጡ ዝርዝር ሰነዶች ለ WT Media (ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ) ደርሰዋል።

አዲሱ ክስ ባለሀብቱ በክልሉ አመራሮች ላይ ‘የዘይሴ ሕዝብን በመደገፍ’ የሚል የሐሰት ክስ ለመመስረት የተሞከረው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ፣ ምንም ጭብጥ የሌለው እና በእስር ላይ ባለ ሰው ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።

አዲሱ የ53 ሺህ ብር ክስ ዝርዝር፦ ከሳሽ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትሕ ቢሮ ሲሆን ተከሳሽ ደግሞ ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ (ዕድሜ 34 ዓመት) ይላል።

የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ባቀረበው አዲስ ክስ መሠረት፣ ባለሀብቱ በሳውላ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ በሚቆይበት ወቅት፣ የጣቢያው አዛዥ ለነበሩት ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጩቱሎን ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማስገኘትና ግዴታውን እንዳይወጣ አድርጓል ተብሏል።

የወንጀል ድርጊት: ኢንጂነር ብርሃነመስቀል፣ የአዛዡ መኖሪያ ቤት የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እንደሌለው በማረጋገጥ፣ ሁለት የእንጨት መብራት ፖል፣ 100 ሜትር የኤሌክትሪክ ገመድ፣ አንድ የመብራት ቆጣሪ ማሽን፣ እንዲሁም ለጉልበት ሥራ ማስገመቻ ገንዘብ እና ሁለት ተለቪዥን በጠቅላላው 53,767 ብር በመክፈል ለአዛዡ ሰጥቷል በሚል ክስ ተመስርቶበታል።

ከዚህ ቀደም በማዕድን ሴራው ምክንያት ክልሉ 12 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ደርሶበታል በሚል በፌዴራል ፍርድ ቤት ሂደት ላይ እያለ የቀረበው ክስ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።

ኢንጂነሩ ከሳውላ ማረሚያ ወደ አርባምንጭ ሲወሰድ፣ “የዘይሴ ሕዝብን በመደገፍ በክልሉ መንግሥት ላይ እንዲነሱ አድርጓል” በሚል ሌላ ክስ ለመክፈት መዘጋጀቱ በ #WTMedia ይፋ መደረጉን ተከትሎ፣ በሕዝብ ዘንድና ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ ትችት በመነሳቱ፣ የጥላሁን ከበደ ቡድን ይህንን ክስ ለመሰረዝ ተገዷል።

አሁን ላይ ደግሞ የክልሉ አመራር ምንም አይነት ሌላ ክስ ማጣት በመላ፣ ባለሀብቱ በእነሱ ጥበቃ ሥር በእስር ቤት ታስሮ እያለ ፈጽሟል የተባለውን የ53 ሺህ ብር “አስቂኝ” ክስ ማምጣቱ፣ ጉዳዩ የሕግ ሳይሆን የፖለቲካ የበቀል ሴራ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

ክልሉ በተደጋጋሚ ወጣቱ ባለሀብት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ በሚል ከፌዴራል ፖሊስና ደህንነት የተላከውን የሕጋዊ ደብዳቤ ትዕዛዝ በመከልከል መመለሳቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይ፣ ባለሀብቱ በማዕድን ክርክር ወቅት ባሳገደበት ቦታ ላይ ሌሎች ባለሀብቶች ገብተው እንዲሠሩ እየተደረገ ሲሆን፣ የፍርድ ቤቱ የእግድ ትዕዛዝ ለማክበር ክልሉ እንቢተኝነት በማሳየቱ ወደኋላ መመለሳቸውን #WTMedia ቀደም ሲል መዘገቡ አይዘነጋም።

በሕግ ባለሙያዎች ጭምር የፖለቲካ የበቀል ሴራ ተብሎ የተገለጸው ይህ አዲስ ክስ፣ የፍትሕ ጥያቄ ወደ ስቃይነት መቀየሩን የሚያሳይ እንደሆነ በርካቶች ይስማሙበታል።

በወጣት ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ላይ የተከፈተውን አዲስ የ53 ሺህ ብር ክስ አስመልክቶ WT Media ያገኘው ተጨማሪ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ክሱ በዋናነት የተመሰረተው ኢንጂነሩን ያስተናገዱት የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ በሆኑት ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጩቱሎ ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ነው።

ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ከአዲስ አበባ ተይዘው ወደ ሳውላ ፖሊስ ጣቢያ ሲገቡ፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና ቡድናቸው የባለሀብቱ ሰብዓዊ መብት እንዲጣስ እና በሰብዓዊነት በማይመጥን ሁኔታ እንዲቆይ ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጩቱሎ ይህንን ትዕዛዝ እምቢ ብለዋል።

ኢንስፔክተሩ የተጠርጣሪውን ባለሀብት ሰብዓዊ መብት በማይጥስ መንገድ እንዲቆይ በማድረጋቸው ምክንያት፣ በአቶ ጥላሁን ከበደ ከስልጣን እንዲታገዱ መደረጉና መታሰሩ ይታወሳል።

የክልሉ ፍትሕ ቢሮ አሁን በኢንጂነር ብርሃነመስቀል ላይ የ53,767 ብር ክስ የመሰረተው፣ ባለሀብቱ በታሰረበት ወቅት ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጩቱሎን ተገቢ ያልሆነ ጥቅም በማስገኘትና ግዴታውን እንዳይወጣ በማድረግ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ነው።

ይህ አነስተኛ ክስ፣ በፖሊስ አዛዡ ላይ ከተወሰደው የስልጣን ማገድ እርምጃ ጋር ተያይዞ ሲታይ፣ የባለሀብቱን ሰብዓዊ መብት በማክበሩ ምክንያት ለተቀጡት ፖሊስ አዛዥ የበቀል ማስፈጸሚያ ለመሆን ያለመ መሆኑን ያጠናክራል።

በክልሉ አመራር ላይ በግልጽ በሙስናና ዝርፊያ የተከሰሰን ሰው ሰብዓዊ መብቱን ማክበር ብቻ የስልጣን መነጠቅና የወንጀል ክስ ምክንያት መሆኑ፣ የክልሉን የፍትሕ ስርዓት አደጋ ላይ መውደቁን ያሳያል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media