GridArt_20251119_151134234

የፕሬዝዳንቱን ህገወጥ ትዕዛዝ ያልተቀበሉት ኮሚሽነር ተባረሩ፤ የፌዴራል ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የካዱት ምክትል ኮማንደር ኮሚሽነር ተደረገው መሾማቸው ተገልጿል።

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እየተፈጸመ ነው የተባለው የፖለቲካ ሴራ እና የአመራር ብልሹ አሠራር የክልሉን ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጭምር ማተራመሱን WT Media ከታማኝ ምንጮች አረጋግጧል።

በተለይ ወጣቱ ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ በእስር ላይ በሚገኝበት ወቅት ሕግን ተላልፎ የተፈጸመው የአመራር ሽግሽግ በስፋት እያነጋገረ ነው።

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ ከችሎት ቀርቦ እንዲከራከር ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ አቶ ጥላሁን ከበደ ትዕዛዙን ከልክለው ባለሀብቱ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ በማድረግ ሕግን ጥሰዋል።

በወቅቱ የክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ፣ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መፈጸም አለበት የሚል ጠንካራ አቋም በማንጸባረቃቸውና የመርህ ሰው በመሆናቸው፣ በአቶ ጥላሁን ከበደ “ሥር በሰደደ የዎላይታ ጥላቻ” ተነክሶባቸው ከአሠራር ውጪ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ከዚህ ቀደም የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እያሉ፣ አቶ ጥላሁን በዘይሴ አካባቢ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም በፈበረከው የሐሰት መረጃ “መከላከያ እንዲገባ ፈርም” ሲሉ፣ “እኔ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ፍጅት አላውጅም” በማለት በግንባር ቀደምትነት መቃወማቸው ከኃላፊነታቸው የመባረራቸው ዋና ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል።

በኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ምትክ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይዘው የመጡ የፌዴራል ፖሊስ አባላትን ላለማግኘት ቢሯቸውን ቆልፈው ስልካቸውን አጠፋፍተው የጠፉት ምክትል ኮማንደር ብርቱኳን መንግስቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

ይህ ሹመት የአቶ ጥላሁን ከበደ ህገ ወጥ ትዕዛዝ በመቀበላቸው የተከፈላቸው ወሮታ መሆኑ ተነግሯል።

አስተያየት ሰጪዎች፣ ምክትል ኮማንደር ብርትኳን አንድ ዓመት እንኳን የሚሞላ የአመራርነት ልምድ የሌላቸው እና ግዙፍ ተቋምን የመምራት ብቃት የላቸዉም ብለዋል።

ከፖሊስ የሥነ-ምግባር አሠራር ውጪ፣ ልምድ ያካበቱና ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸውን ኮሚሽነሮች፣ ምክትልና ረዳት ኮሚሽነሮችን ሽቅብ ተንጠራርታ እንድትመራ መፈቀዱ፣ “ከሌብነትና በጥቅም መተሳሰር የመጣ፣ የርዕሰ መስተዳድሩን ዕውቀት አልባነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ከኃላፊነት የተነሱበት ሌላኛው ምስጢር፣ በክልሉ በጅምር የቀሩ የጊዶሌ፣ የአርባምንጭ፣ የሶዶ እና የዲላ ማረሚያ ቤቶች ግንባታን “በቁርጥ ዋጋ” ለሚፈልጓቸው ሰዎች ለመስጠት የወጠኑትን የጥላሁን እቅድ፣ “የሕዝብ ሃብት አይዘረፍም” ብለው ፊት ለፊት ሞግተው ማዋረዳቸውና የቀረበውን ዋጋ አላጸድቅም ማለታቸው መሆኑ ተገልጿል።

የጥላሁንን ሴራ የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች፣ የምክትል ኮማንደሯን ሹመት “ርዕሰ መስተዳድሩ ሴት አመራሮችን እያማገጠ ወደ ሥልጣን የመጎተት አባዜ” እንደሆነ በመጠቆም የመጀመሪያው ጥርጣሬያቸውን አስቀምጠዋል።

ሁለተኛው ትንተና ደግሞ፣ የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጩቱሎ ኢንጂነር ብርሃነመስቀልን ሰብዓዊ መብቱን በማክበር ከማሰቃየት ትዕዛዝ እምቢ ማለታቸውን ተከትሎ በሳውላ ከተማ ላይ ተቃውሞ በመነሳቱ የጠለሸውን ስሙን ለማደስ የሄደበት ርቀት ነው የሚል አስተያየትም ቀርቧል።

ሴረኛው ጥላሁን ከበደ በሰሞኑ የፓርቲ ስልጠና በኋላ በሚጠራው አስቸኳይ የምክር ቤት ጉባኤ ይወገዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ምንም እንኳን የአፋሩን ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ አወል አርባን ጨምሮ ሌሎችንም ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽምግልና ቢልክም፣ በዎላይታ፣ ጋርዱላ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂና ኮሬ እንዲሁም አሌ ዞኖች ባደረሰው በደል ምክንያት “ካለአቅሙ ከተቀመጠበት የክልሉ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ይፈጠፈጣል” የሚል ግምት አለ።

“ሴረኞች ይሽመደመዳሉ፤ ሌቦች ይዋረዳሉ፤ ሕዝብ ግን ምን ጊዜም ባለ ድል ነው! ፍትህ ያለ ወንጀሉ በፖለቲካ ሴራ ለወራት ታስሮ ለሚሰቃየው ወጣቱ ባለሀብት ኢንጂነር ብርሃነመስቀል ክንፈ” መልዕክት ተላልፏል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media