ከአሸባሪው ህወሓት የተቃጣብንን ትንኮሳና ጦርነት፤ ዕድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናት ለጦርነት የመመልመሉን ተግባር በማውገዝ ለመከላከያ ሰራዊቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚሰጥ የሚያረጋግጥ ህዝባዊ ሰልፍ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እየመከተ ላለው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሰልፈኞች ገልጸዋል፡፡
ከዞኑ ከሁሉም ወረዳ/ከተማ አስተዳዳር የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ ወጥተው መከላከያ ዝና የሚገልጹ የተለያዩ መፈክሮችን ይዞ እየተሳተፈ ይገኛል።
ከመፈክሮቹም ጥቅቱ “ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሃናችንን ለማድመቅ እንሠራለን፤ የአሸባሪውን የህወሃት ትንኮሳ እናከሽፋለን፤ ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ሃያል ናት፤ ብሔራዊ ጥቅማችን እና ሉዓላዊነታችን ይከበር፤ እኔ የጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ደጀን ነኝ፤ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ ደማቅ አሻራችን ነው ፤ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች፤ጦር መሣሪያ ከትግራይ ህፃናት ትከሻ ይውረድ ፤ክብርና ሞገስ ለመላው የፀጥታ ሀይላችን የሚሉና” ሌሎች የተለያዩ መፎክሮችን በመያዝ ድጋፋን እያሰሙ ይገኛሉ።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 14/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
