በዞኑ ከአየር ንብረት መዛባት ጋር ተያይዞ በዋናነት ከሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች የጎርፍና የመረት ናዳ አደጋዎች ዋና ዋናዎቹ መሆኖቸውን የመምሪያው መረጃ ያመላክታል፡፡
በእነዚህ አደጋዎች ምክንያት ዓምና በርካታ ንብረቶች የወደሙ ሲሆን የ8 ሰዎች ነፍስ የጠፋ መሆኑንም የዎላይታ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ኀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማሪያም ገለጹ፡፡
በኪንዶ ዲዳየ ፣በካዎ ኮይሻ፣ ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳዎች አከባቢ የሚገኙ አንዳንድ ቀበሌያት የመሬት አቀማመጥ ተራራማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አምና በክረምት ወቅት በተከታታይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ የመሬት መንሸራተት በመከሰቱ የአደጋው ሰለባ የነበሩ አካባቢዎች መሆናቸውን አቶ ጴጥሮስ አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል ከአባላ አባያ ወረዳ ጫው ካሬ ቀበሌ፣ ከዳሞት ወይዴ ወረዳ ቶራ ሳዴቦ፣ ከድጉና ፋንጎ ብላቴ ጫርቾ፣ እና ከሆብቻ ወረዳ ሆብቻ ባዳ ቀበሌያት ደግሞ በጎርፍ የተጠቁ አካባቢዎች መሆናቸውን ኃላፊው አያይዘው አክለዋል፡፡
በአደጋው በአጠቃላይ 5 ሺህ 595 አባወራ እና በቤተሰብ 41 ሺህ 465 የሚያህል ለጉዳት መዳረጋቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጴጥሮስ በ2013 ዓ/ም ክረምት ወቅትም ተመሳሳይ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል የሚያሳይ የዝናብ ሁኔታ ትንቢያ ስላለ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አቶ ጴጥሮስ አበክረው አሳስበዋል።
ከኢለኪኖ/ላኒኖ ተጽዕኖ የአየር ንብረት ስርዓት መዛባት ጋር ተያይዞ በተለምደው የዝናብ መጠን ያለመዝነብና ቢዘንብም መጠኑ እጅግ የበዛ ወይም የቀነሰ በመሆን ዞናችን በተጽዕኖው ስር እንዲወድቅ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
አሁን የሚንገኝበት የአየር ንብረት ሁኔታ እጅግ ተለዋዋጭ በመሆኑ የተቀናጀና የተጠናከረ ሥራ በመስራት ሊደርስ የሚችለውን ሰብአዊና ቁሳዊ ቀውስ ለመቀነስ መረባረብ እንደሚገባ አቶ ጴጥሮስ ገልጸዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል፡፡
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 14/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
