GridArt_20251130_174518514

ለፍትህ የታገለ የህዝብ ባለውለታ ልጅና ባለቤት በአደባባይ ፍትህ በማጣት እየተሰቃዩ ዝምታው ለምንድነው ?

WT Media ከ2 ቀን በፊት በቪዲዮ መረጃ አስደግፎ እንደዘገበው ወ/ሮ መክሊት ዳባራ፣ ባለቤታቸውን ባለሀብት ብርሃነመስቀልን ለመጠየቅ በአርባምንጭ ከተማ በቆየችበት ወቅት በሆቴል አልጋዋ ላይ በታጠቁ ኃይሎች ጉዳት ለማድረስ መሞከሩን ተከትሎ፣ ይህ ድርጊት በሕዝብ ተወዳጅና በጎ አድራጊ ባለሀብት ላይ የታወጀ የፍትህ መዛባትና የልማት ኃይልን የማምከን ሴራ ተደርጎ በጽኑ ተወግዟል።

WT Media የታሰረው ባለሀብትና የቤተሰቡን ዳራ በማጣመር፣ የሕዝቡን አቋም የሚያንጸባርቀውን ዝርዝር ዘገባ እንደሚከተለው አቅርቧል።

የወ/ሮ መክሊት አባት አቶ ደባራ ሜጊሶ (ከዎላይታ አውራጃ) ከወጣትነታቸው ጀምሮ ለሕዝብ ጥቅምና ፍትህ ሲታገሉ የኖሩ አባት ናቸው።

አቶ ደባራ ሜጊሶ የበሌ ሃዋሳ ከተማን ከመቆርቆር ጀምሮ የልማት ሥራዎችን ያስተዋወቁ ፈር ቀዳጅ አርበኛ ነበሩ።

በሕዝብ ወገንተኝነት ምክንያት በዘመነ ደርግ የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው በሕዝብ ምስክርነት ከመዳናቸው ባሻገር፣ ለዎላይታ ወጣቶች ትምህርትና ለዎጋጎዳ የዞን ጥያቄ ትግልን የመሩ ታላቅ ሰው ነበሩ።

አሁን የዚህ ታላቅ አባት ልጅ ወ/ሮ መክሊት፣ በባለቤቷ ላይ በተመሠረተ የሙስና ማስገደል ሴራ ሳቢያ፣ “ባረፈችበት ሆቴል ላይ” በታጠቁ ኃይሎች ለጥቃት መጋለጧ “የታገሉለት የፍትህ ዓላማ ተቃርኖ የመጣበት ዘመን ነው” በሚል በጽኑ ተወግዟል።

ባለሀብት ብርሃነመስቀል (ትውልዱ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ትውልድ ቦታ ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ነው) በአካባቢው በጎ ተግባር የሚታወቅና ለልማት ከፊት የሚሰለፍ ተወዳጅ ሰው ነበር።

ብርሃነመስቀል በንግድ ሥራው ባፈራው ሀብት በርካቶችን የስራ ዕድል እንዲያገኙ ያደረገ ሲሆን፣ አሁንም በርካታ አዳዲስ የልማት ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት ነው ሆን ተብሎና በሴራ የታሰረው።

ባለሀብቱ በቁጥጥር ስር የዋለው የአቶ ጥላሁን ከበደ የሙስና ቅሌት ማጋለጡን ተከትሎ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።

ይህም በሕዝቡ ዘንድ “ፍትህ የሙሰኞች መሳሪያ ሆኗል” የሚል ሰፊ ጥርጣሬ ፈጥሯል።

በወ/ሮ መክሊት ዳባራ ላይ የተደረገው ጥቃት፣ በታሰረው ባለሀብት ላይ የሞት ፍርድ ለመፍረድ የታቀደ ሴራ አካል ሊሆን ይችላል የሚል አስደንጋጭ ትንተና ቀርቧል።

በሆቴል አልጋዋ ላይ “በር ካልከፈትሽ” በሚል ታጥቀው መግባታቸው፣ “ባለሐብቱን በምግብ መርዘው ለመግደል ስላሰቡ ምስቱ ስንቅ እንዳታቀርብ ለማድረግ” ይሆናል የሚል ስጋት አስቀምጠዋል።

ይህ ደግሞ ታሳሪውን በቀላሉ እንዲያስገድል በፖለቲካዊ ፍላጎትና ሙስና የታገዘ የመዋቅር ወንጀል መሆኑ ተገልጿል።

ወ/ሮ መክሊት “ሕፃን ልጅ ይዤ በዚህ ሰዐት? ህዝብ ይወቅልኝ። መንግስትም ይስማ” በሚል ያስተላለፈችው የሕይወት ስጋት ጥሪ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሕግ የበላይነት መጥፋቱን በግልፅ የሚያሳይ ነው።

የዎላይታ ተወላጆች፣ በሕዝብ ተወዳጅ፣ ለልማት ተፋላሚና የስራ ፈጣሪ በሆነ ባለሀብት ላይ፣ የፖለቲካ ሙሰኞች ሴራ በመፈጸማቸው፣ ይህም ሥርዓቱ ራሱ አደጋ ላይ መውደቁን ያመለክታል በሚል በጽኑ አውግዘዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጉዳዩን በቸልተኝነት ማየታቸው በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥርጣሬ መፍጠሩን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።

ሙሰኞች በሕግ የተደገፈ ግፍ እንዳይፈጽሙ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ያለውን ብሔር ተኮር ጥቃት እና ሙስና በአስቸኳይ እንዲቆም፣ እንዲሁም ወ/ሮ መክሊትንና ባለቤቷን ጨምሮ የዜጎች ደህንነት እንዲረጋገጥ የአፋጣኝ እርምጃ ጥሪ ቀርቧል።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media