1000088491

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ቀጣዩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በዋና ጸሐፊነት እንዲመሩ ከአሜሪካ፣ ከእስራኤልና ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለመወዳደር ፍላጎት ማሳየታቸው ተሰማ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (#ተመድ) መሪነት እንዲወዳደሩ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት እየተደረገ ባለበት ይፋዊ የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍም ይጠበቃል ተብሏል።

ይህንን ታሪካዊ እጩነት በይፋ ለማጽናት ግን አሁን የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍና የእጩነት ደብዳቤ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

ከ Ethio Insight መረጃ ተጨማሪ WT Media ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሠረት፣ አሜሪካ ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ይፋዊ የውድድር ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን፣ እስራኤልና ስማቸው ያልተጠቀሰ የአውሮፓ ሀገራትም ይህንንኑ ጥያቄ ደግፈውታል። 

አቶ ኃይለማርያም በበኩላቸው፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት አመኔታቸውን ከጣሉባቸውና ይሁንታ ከሰጡ ድርጅቱን በሃላፊነት ለመምራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

እንደ ሩዋንዳ ያሉ የአፍሪካ ሀገራትም በአቶ ኃይለማርያም እጩነት እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎችም ድጋፋቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊነት ውድድር በይፋ የተጀመረው እ.ኤ.አ November 25, 2025 ሲሆን፣ ሂደቱ የሚከተሉትን ቁልፍ ቀናት ያካትታል፡-

April 1, 2026፡ የእጩነት ደብዳቤ የሚገባበት የመጨረሻው ተመራጭ ጊዜ። እጩዎች እስከዚህ ቀን ድረስ ደብዳቤያቸውን ካስገቡ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ በቂ ጊዜ ያገኛሉ።

June 2026፡ እጩዎች በተለያዩ መድረኮች ራሳቸውንና ራዕያቸውን የሚያስተዋውቁበት ወቅት።

 የ2026 ማብቂያ፡ የጸጥታው ምክር ቤት እጩውን ለጠቅላላ ጉባኤው የሚያቀርብበትና ጉባኤው ድምፅ የሚሰጥበት ወቅት።

January 1, 2027፡ አዲሱ ዋና ጸሐፊ ሥራውን የሚጀምርበት ቀን ነው።

ምንም እንኳን አንድን እጩ ማንኛውም አባል ሀገር ወይም የሀገራት ስብስብ ሊያቀርብ ቢችልም፣ ከሀገር ክብርና ከአንድነት አንፃር የእጩነት ጥያቄው ከትውልድ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ቢቀርብ ተገቢና ውጤታማ እንደሚሆን ብዙዎች ይስማማሉ። 

የኢትዮጵያ መንግስት የእጩነት ደብዳቤውን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚያስገባ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን እያሉ ያስመዘገቡት ዲፕሎማሲያዊ ስኬት፣ ከስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር መልቀቃቸውና ከዚያ በኋላም በሰላም፣ በአየር ንብረት ለውጥና በልማት ዘርፎች ያሳዩት ብቃት፣ ለቦታው ብቁ ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል። ይህ እጩነት በመላው ኢትዮጵያም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ወርቃማ እድል በመጠቀም፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ለውድድሩ የተሟላ ዝግጅት እንዲያደርጉና የሀገሪቱን ገፅታ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ እንዲያደርጉ የበኩሉን ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

#HailemariamDesalegn #UNSG #UNGA #Ethiopia #GlobalLeadership #Statesmanship #HailemariamForUN #UNSecretaryGeneral2027 #SupportHailemariam