ለግንባታው የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ
የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ አገልግሎት የዎላይታ ድስትሪክት በሶዶ ከተማ ከዚህ በፊት አገልግሎት እየሰጠ ባለበት በተለምዶ 21 ማዞሪያ(ቆቃ ሰፈር) አከባበቢ ከስድስት ሺህ በላይ ካሬ መሬት ላይ ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ባለሰባት ፎቅ ህንፃ በከተማዋ ለመገንባት የሚያስችል መሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓት የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ተከናውኗል።
የህንፃው ግንባታ በአጭር ጊዜ ተጠናቅቆ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚደረግ መሆኑም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ድስትሪክት ባለባቸው ከተሞች ተመሳሳይ ባለሰባት ፎቆ ስድስት ህንፃዎች እንደሚገነቡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 19/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
