1000091029

በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ባጋጠመው የናፍጣ አቅርቦት እጥረት ምክንያት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ገለጹ።

ችግሩ በተለይ በዎላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በሀዋሳ፣ በዲላ እና በአርባ ምንጭ ከተሞች በከፋ ሁኔታ መታየቱ ታውቋል።

አሽከርካሪዎች እንደገለጹት፣ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ናፍጣ ለማግኘት በየማደያዎች ከሁለት እስከ አራት ቀናት ለመሰለፍ ተገድደዋል።

ይህ መስተጓጎል በተለይ፦ የህዝብ ተጓዦችን ለማጓጓዝ እና የሸቀጥ ምርቶችን ወደ መሀል ሀገር ለማስገባት ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

አንዳንድ አሽከርካሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ የነዳጅ አቅርቦቱ “በማደያዎች በጎ ፈቃድ ላይ የወደቀ” መሆኑን ገልጸዋል።

“ከፈለጉ ይቀዱልናል፤ ካልፈለጉ ደግሞ ‘ነዳጅ የለም’ በሚል ምክንያት ሰልፉን ይበትኑታል” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

የተሽከርካሪ የህዝብ እንቅስቃሴው ይበልጥ እየተገደበ መሆኑን የገለጹት ባለሙያዎች፣ የሚመለከተው የመንግስት አካል በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያለውን ችግር ፈጥኖ እንዲፈታ አሽከርካሪዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።