1000092789

በክልሉ የጌዴኦ ዞን መቀመጫ በሆነችው የዲላ ከተማ እና በቡሌ ወረዳ መካከል ባለው የትራንስፖርት መስመር፣ ተሳፋሪዎች በሕገ-ወጥ የታሪፍ ጭማሪና ለአደጋ በሚያጋልጥ አጫጫን ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን WT Media ያደረገው የመስክ ቅኝትና ያሰባሰባቸው መረጃዎች አመላክተዋል።

መንግሥት ምንም ዓይነት የታሪፍ ማሻሻያ ባላደረገበት ሁኔታ፣ አንዳንድ አሽከርካሪዎችና ባለቤቶች የሕዝቡን ስቃይ መነገጃ አድርገውታል።

ቡሌ ከተማ መናሀሪያ

በትላንትናው ዕለት እና ዛሬ በመናኸሪያ ውስጥ የታዘቡት የአይን እማኞች የሚከተሉትን አሽከርካሪዎች በስም በመጥቀስ ቅሬታ አቅርበዋል፦

የሕዝብ ታሪፍ 89 ብር ሆኖ ሳለ፣ ያላንዳች እፍረት 150 ብር ሲሰበስብ ውሏል። የታሪፍ ጭማሪው ይብስባቸዋል፤ ከሕዝብ 200 ብር በመቀበል ሕገ-ወጥ ብዝበዛ እያካሄዱ ይገኛሉ።

ከተቀመጠው ታሪፍ ውጭ 150 ብር በማስከፈልና ተሳፋሪን በማንገላታት ተጠቅሰዋል።

የመኪና መናሀሪያ

የቡሌ መንገድ ተጓዦች እንደሚሉት፣ አሽከርካሪዎች መኪናውን ወደ መናኸሪያ ከማስገባታቸው በፊት በወንበሮች ሥር የአልኮል መጠጦችን ይደብቃሉ።

በመናኸሪያው ውስጥ ተሳፋሪዎችን “እንደ እህል” አፍነው ከጫኑ በኋላ፣ በግንብ ውስጥ ተደብቀው ተጨማሪ ሸቀጣሸቀጦችን (ዱቄት፣ ስኳር፣ ቲማቲም) ይጭናሉ።

ይህ አይነቱ አጫጫን የመኪናውን ሚዛን ስለሚያዛባ፣ በዳገትና ቁልቁለት በበዛበት የቡሌ መንገድ ላይ ለተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋና ለሕይወት መጥፋት ምክንያት እየሆነ ይገኛል።

መናሀሪያ

በጣም የሚያሳዝነውና ነዋሪዎቹን ያስቆጣው ጉዳይ፣ የሕዝብን ደኅንነት እንዲጠብቁ የተመደቡ የትራፊክ ፖሊሶች ድርጊት ነው።

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ፣ አንዳንድ ትራፊኮች አደገኛ አጫጫኑንና ሕገ-ወጥ ጭነቱን እያዩ፣ በ 200 ብር “ድብቅ ስጦታ” አይናቸውን ይጨፍናሉ።

እናቶች፣ ነፍሰጡሮች፣ አዛውንቶችና አካል ጉዳተኞች በመኪና ውስጥ ታፍነው ሲሰቃዩ እያዩ፣ ትራፊኮቹ ለሰው ሕይወት ሳይሆን ለጥቅማቸው በማደላታቸው ሕዝቡ “ለማን አቤት ይባላል?” ሲል ምሬቱን ገልጿል።

WT Media በዲላ ከተማ መናኸሪያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ይህን ከፍተኛ እንግልትና ሕገ-ወጥ አሠራር አስመልክቶ የዲላ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሠራተኞችንና ኃላፊዎችን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም፣ በኃላፊዎቹ በኩል ምንም ዓይነት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

ይህ የአመራሮች ቸልተኝነትና ኃላፊነትን የመሸሽ ተግባር አሽከርካሪዎቹ ተሳፋሪውን ይበልጥ እንዲበዘብዙ ዕድል ሰጥቷቸዋል።

WT Media የሚመለከታቸው የዞንና የክልል የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ አካላት በእነዚህ በዝባዦችና ጉቦ ተቀባይ ትራፊኮች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ይጠይቃል።

️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን

Voice of Marginalized Community – WT Media