GridArt_20260226_202318913

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ዞን፣ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ የዘይሴ ብሔረሰብ አባላት ላይ በታጠቁ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና መደበኛ ባልሆኑ ቡድኖች የተቀናጀ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ዘረፋና ማፈናቀል  እየተፈጸመ መሆኑን WT Media ከነዋሪዎች፣ ከአይን እማኞችና በቪዲዮ ከተደገፉ መረጃዎች አረጋግጧል።

ከባለፈው ሳምንት ጥቃት በኃላ በድጋሚ ከየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኦቶራ፣ በማዣ እና በአጎሌ ቀበሌዎች የደቡብ ክልል ልዩ ኃይልና የጋሞ ዞን ፖሊሶች በከፈቱት ጥይት በርካታ ንጹሐን ተገድለዋል።

እንደ አከባቢው ነዋሪዎች ገለፃ ከሆነ አቅም ያላቸው ወጣቶች ሸሽተው ሲያመልጡ፣ መሮጥ የማይችሉ አረጋውያንና አቅመ ደካሞች በጭካኔ ተረሽነዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ 8 ወጣቶች ተሰልፈው የተረሸኑ ሲሆን፣ የሀገር ሽማግሌዎች በገጀራ አንገታቸው ተቀልቷል። በአጠቃላይ ከ30 በላይ ንጹሐን ደም በከንቱ መፈሰሱ ተረጋግጧል።

ጥቃቱ በሰው ሕይወት ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ የብሔረሰቡን የኢኮኖሚ መሠረት ለማውደም የታቀደ ይመስላል።

በላማጰ፣ በበካይበና፣ በጋለፋ እና በመይጫ አካባቢ የሚገኙ ቤቶች ከነሙሉ ንብረታቸውና የእህል ጎተራዎቻቸው በእሳት እንዲጋዩ ተደርገዋል።

የላጎ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን ተሰብሮ በመግባት ንብረቱ ተዘርፏል፤ የሙዚቃ መሣሪያዎችና መድረኮች ተሰባብረዋል።

የወዜቃ የዘይሴ ሰበካ ጽሕፈት ቤትና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤትም በተመሳሳይ ሙሉ በሙሉ ተዘርፈው ወድመዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዘይሴ ሕዝብ ላይ የተቀናጀ የረሃብ እና የውሃ ጥም ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል፦

የውሃ ቧንቧዎች የተዘጉ ሲሆን፣ ወደ ዘይሴ የሚፈሱ ወራጅ ውሃዎች አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል። ከብቶች እንኳ የሚጠጡት ውሃ አጥተው እንዲረግፉ ተፈርዶባቸዋል።

የብሔረሰቡ ዋነኛ ገቢ የሆነው የአርባምንጭ ሙዝ ወደ ገበያ እንዳይወጣ በመከልከሉ በማሳው ላይ እየበሰበሰ ይገኛል።

ወፍጮ ቤቶች ተዘግተዋል፤ የሞባይል ካርድ ሽያጭ እንኳ እንዳይኖር በማድረግ ሕዝቡ ከዓለም ጋር እንዳይገናኝ ተደርጓል።

ይህ ጭፍጨፋ በከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች የሚመራና ድጋፍ የሚሰጠው መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና ሌሎች የጋሞ አመራሮች፣ የዘይሴ ተወካይ የሆኑት አቶ አብርሃም አሞሼ በፓርላማ የሕዝቡን ድምፅ እንዳያሰሙ በማገድ ጭፍጨፋው ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል እያደረጉ ነው ተብሏል።

የክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ አማንያስ ከሥራ ተባረውና ለእስር ተዳርገው አሁን ለሕይወታቸው በመስጋት መሰደዳቸው ታውቋል።

የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ታደሰ “በዘይሴ ላይ የጀመርነው ጭፍጨፋ ተጠናክሮ ይቀጥላል” በማለት በግልጽ መዛታቸውን እማኞች ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት 60 የሚጠጉ ሰዎች ታፍነው የት እንደደረሱ አይታወቅም። የዘይሴ ብሔረሰብ ሙሉ በሙሉ ተፈናቅሎ በሜዳ ላይ ወድቋል።

WT Media ይህንን በተከታታይ እየተፈጸመ ያለውን የተደራጀ የዘር ማጥፋት (Genocide) ዘመቻ በጽኑ ያወግዛል።

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የፌዴራል መንግሥት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብተው ይህንን የንጹሐን ደም እልቂት እንዲያስቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏

Voice of Marginalized Community – WT Media