ከሐምሌ1/2013 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም በሚፈፀመው አንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከክልል መንግስት ከሚሰበሰበው ገቢ፣ ከፌዴራል መንግስት ድጎማና ከሌሎች የገቢ ምንጮች ከሚገኘው ገንዘብ እንደሆነ ረቂቅ የበጀት አዋጁን ያቀረቡት የክልሉ ምክር ቤት የበጀት ፋይናንስና ኦዲት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስራት አበበ ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት:-
1, ለክልል ማዕከል መ/ቤቶች መደበኛና ካፒታል ወጪ 4,190,333,908
2,ለዘኖች፣ ልዩ ወረዳዎች ጥቅል በጀት 39,226,993,625 ብር
3, ለክልላዊ ፕሮግራሞች 3,495,614,890
4,ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ 1,930,560,000
5, ለክልሉ መጠባበቂያ በጀት 200,000,000 ብር ።
በአጠቃላይ የ2014 በጀት ዓመት የክልሉ መንግስት በጀት49,043,502,423 (አርባ ዘጠኝ ቢሊየን አርባ ሶስት ሚሊየን አምስት መቶ ሁለት ሺ አራት መቶ ሀያ ሶስት ብር) ሆኖ በ 6 ድምፀ ታቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።
የፀደቀው 49 ቢሊየን 43 ሚሊየን 502 ሺ 423 ብር በክልሉ በበጀት አመቱ ለተያዙ የትምህርት፣ ጤና፣ የመሰረተ ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ዋና ዋና የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ የሚውል ነው መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ረቂቅ በጀቱን ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት አብራርተዋል::
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክWolaita Timesme/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 26/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹


