በ21ኛው ክፍለ ዘመን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አብዛኛው ገጠራማ አካባቢዎች የመንገድና የድልድይ መሠረተ ልማት ባለመኖሩ፣ ዜጎች ለሞትና ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ።
WT Media ከበርካታ ቦታዎች ከደረሱት መካከል ለማሳያነት የቀረበው ከጎፋ እና ከቡርጂ ዞኖች ያሰባሰባቸው ምስሎችና መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ሕዝቡ በራሱ አቅም በሠራቸው አደገኛ የእንጨት ድልድዮች ላይ እናቶችን በቃሬዛ ተሸክሞ ለሰዓታት በመጓዝ ወደ ጤና ተቋማት ለማድረስ ይታገላል።



በክልሉ ለጤና አገልግሎትና ለድንገተኛ አደጋ ተብለው የተመደቡ አምቡላንሶች፣ በብዙ አካባቢዎች ለባለሥልጣናት የግል ጉዳዮችና ለቢሮ ሥራዎች መገልገያ እየዋሉ መሆኑን ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ።
በዚህም ምክንያት፦ ምጥ የያዛቸው እናቶች ወደ ጤና ተቋም ለመሄድ አምቡላንስ ማግኘት የማይታሰብ ሆኗል።
ቤተሰብና ጎረቤት እናቶችን በቃሬዛ ተሸክመው በዱር በገደሉ እንዲጓዙ ተገደዋል።
ምስሉ እንደሚያሳየው፣ ሕዝቡ በወንዞች ላይ በራሱ አቅም የሠራቸው ድልድዮች እጅግ አደገኛና ለሕይወት ስጋት የሆኑ ናቸው።




እናቶችን ተሸክመው በእነዚህ ጠባብ እንጨቶች ላይ የሚሻገሩ ወጣቶች፣ አንዲት ስህተት ቢሰሩ እናቲቱንም ሆነ የተሸካሚዎቹን ሕይወት ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው።
“በዚህ ሁሉ ስቃይ አልፋ ልጇን ታቅፋ ወይንም ለራሷ ተርፋ የምትመለስ እናት ዕድለኛ ነች” ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች። ብዙዎች ግን መንገድ ላይ ሕይወታቸው ያልፋል።
ክልሉ ትኩረቱ በመሠረተ ልማት ላይ መሆን ሲገባው፣ አመራሮቹ አብዛኞቹ በውስጥ ሽኩቻና በጥቅም ትስስር ሙስና መጠመዳቸው እንዲህ ያሉ አንገብጋቢ የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳያገኙ አድርጓል።
በጎፋና በቡርጂ ዞኖች የሚታየው ይህ ምስል የክልሉን ትክክለኛ ገጽታና የባለሥልጣናቱን ግድየለሽነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
የእናቶች ሞት የሚቀነሰው በወረቀት ላይ በሚጻፍ ሪፖርት ሳይሆን፣ እናቶች በቃሬዛ የሚሸከሙበትን መንገድና ድልድይ በመገንባት ነው።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ለአምቡላንሶች አግባብ ያልሆነ አጠቃቀም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግና ለገጠራማው ሕዝብ የመንገድ ግንባታ ቅድሚያ እንዲሰጥ WT Media በጥብቅ ያሳስባል።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media