የወረዳ መዋቅሮችን የሚያገናኝ መንገዶች መበላሸት ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብና ተጎጂዎችን ለህክምና ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ መሆኑም ተገልጿል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን መጀመሪያ ላይ ይህንን አሳዛኝ አደጋ በገጹ ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ዘግቦት የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ ግን ያለምንም ማብራሪያ መረጃውን ከገጹ ላይ አጥፍቶታል።
WT Media ከአካባቢው ምንጮች ባደረገው ማጣራት መረጃው ትክክለኛ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ እንዲህ ያለውን የሕዝብ መከራ ደብቆ ለማለፍ መሞከር ተገቢ አለመሆኑን ይገልጻል።


በዚሁ ወቅቱን ባልጠበቀ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ የሰው ሕይወት ማለፉንና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን WT Media አረጋግጧል።
በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ፣ የላ ቀበሌ (ኮሬ ተብሎ በሚጠራው መንደር) ትናንት ሌሊት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአንድ ቤተሰብ ሦስት አባላት ሕይወት አልፏል።
አንዲት እናትና ሁለት ልጆቻቸው ሕይወታቸው በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል። ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል ስጋት አለ።
የቤተሰቡ አባወራ በከባድ የመቁሰል አደጋ ምክንያት በጋዜሶ ጤና ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና እየተደረገላቸው ቢሆንም፣ መንገዶች በመዘጋታቸው ወደ ተሻለ ሕክምና ማድረስ አልተቻለም።
ከአርባ ምንጭ – ጊና – ቦንኬ የሚያገናኘው ዋና መንገድ በሁለት ቦታዎች በመበላሸቱ ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብና ተጎጂዎችን ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ሆኗል።
መንግሥት በአፋጣኝ መንገዶቹን እንዲከፍትና ለተጎጂው አባወራ የሕክምና ድጋፍ እንዲያመቻች ነዋሪዎች እየተማጸኑ ይገኛሉ።
በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ በጣለው ኃይለኛ ዝናብ ምክንያት በመኖሪያ ቤቶችና በንግድ ተቋማት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።




የጎርፍ መፋሰሻ ቦዮች (ዲቾች) ባለመኖራቸውና ያሉትንም በወቅቱ ባለመጥረጋቸው ጎርፉ ወደ ነዋሪዎች ቤት በመግባት ከፍተኛ ንብረት አውድሟል።
በክልሉ እንዲህ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች በየጊዜው የሚከሰቱ ቢሆንም፣ የክልሉ መንግሥት ቅድመ ጥንቃቄና ዝግጁነት ላይ መሥራት ባለመቻሉ ዜጎች ለሞትና ለንብረት ውድመት እየተዳረጉ ነው።
አሁንም የዝናብ ሁኔታው አሳሳቢ በመሆኑ፣ ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የሚመለከታቸው አካላትም ለአደጋው ተጎጂዎች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media