GridArt_20260316_170512397

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዎላይታ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች የየካቲት ወር ደመወዝ ባለመከፈሉ ምክንያት ከፍተኛ ቅሬታቸውን ለመግለጽ በአሁኑ ሰዓት በዞኑ አስተዳደር ቢሮ ደጃፍ ላይ ተገኝተዋል።

ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡት እነዚህ ሠራተኞች፣ ከመደበኛ የሥራ ገበታቸው ተለይተው አቤቱታቸውን ለማቅረብ ቢመጡም እስካሁን የሚያናግራቸው አመራር ማጣታቸውን ለ WT Media ገልጸዋል።

ሠራተኞቹ ከጧት ጀምሮ በአስተዳደሩ ደጅ ቢቆሙም፣ አንድም የዞን አመራር ወጥቶ ምላሽ ሊሰጣቸው አልቻለም።

“ለኑሮ ውድነቱና ለቤተሰብ አስተዳደር ዋነኛ መተዳደሪያ የሆነው ደመወዝ ባለመከፈሉ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል” የሚሉት ሠራተኞቹ፣ ኃላፊነት የሚሰማው አካል ማጣታቸው ይበልጥ እንዳስቆጣቸው ጠቁመዋል።

በቦታው የተገኙ ሠራተኞች እንዳሉት፣ በዞኑ የሚገኙ የመንግሥትም ሆኑ ሌሎች የአካባቢ ሚዲያዎች ይህንን ግዙፍ ሕዝባዊ ቅሬታ እያዩ እንዳልታየ በማለፍና ከምንም ባለመቁጠር ቸልተኝነት እያሳዩ ይገኛሉ።

ይህ ሚዲያዊ ወገንተኝነት የታጣበት አካሄድ የሠራተኛውን ጩኸት እንዳይታነቅ አድርጓል ተብሏል።

WT Media የሠራተኞቹን አቤቱታ አስመልክቶ የዎላይታ ዞን አስተዳደርን ለማግኘትና ምላሽ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም፣ እስካሁን ድረስ ከአስተዳደሩ በኩል ምንም ዓይነት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

ሠራተኛው የልፋቱን ዋጋ እንዲያገኝና የደመወዝ ክፍያው እንዲፈጸም፣ እንዲሁም ኃላፊነት ያለባቸው አመራሮች ወጥተው ለሕዝቡ ማብራሪያ እንዲሰጡ እያሳሰበን የሠራተኛውንና የጭቁኑን ማኅበረሰብ ድምፅ ማስተጋባቱን ይቀጥላል።