በክልሉ ጎፋ ዞን፣ በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ እንቅስቃሴ እያደረጉ ባሉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮችና አባላት ላይ ያነጣጠረ እስርና ድብደባ መፈጸሙን WT Media አረጋግጧል።
በደምባ ጎፋ ወረዳ አስተዳደር ስር በሚንቀሳቀሱ የፓርቲው አባላት ላይ ጥቃቱ የተፈጸመ ሲሆን፣ በዚህም መምህር ኢሳያስ (የፓርቲው አባል) እና አቶ ስንታየሁ ዳምጠ (የኢዜማ የጎፋ ዞን ማስተባበሪያ ምክትልና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጸሐፊ) ጽኑ ድብደባ ደርሶባቸዋል።
ተጎጂዎቹ በአሁኑ ሰዓት በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ገብተው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ድብደባው በወረዳው ፖሊስ አባላት የተፈጸመ ሲሆን፣ ጥቃቱን በመምራትና በማስፈጸም ረገድ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ቀጥተኛ ትዕዛዝ እንዲሁም የላይማ ፃላ የከተማ ቀበሌ አመራሮች እጅ እንዳለበት ተጎጂዎቹ ለ WT Media ገልጸዋል።
ከድብደባው በተጨማሪ፣ ሌሎች የፓርቲው አባላት “አባል በመሆናቸው ብቻ” ያለ ምንም ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ታውቋል።
ይህ ድርጊት በምርጫ ክልሉ ውስጥ ባሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ደጋፊዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ ምርጫው በነፃነትና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመካሄዱን ጉዳይ አጠራጣሪ አድርጎታል።
WT Media ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም፣ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።
የክልሉ መንግሥትና የምርጫ ቦርድ በጎፋ ዞን እየተፈጸመ ያለውን ይህንን ሕገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲመረምሩና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ጠይቋል።
🎙️ ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media
R