የስታዲየም ግንባታ ወይስ የውሃ ጥያቄ - WT Media ከፍተኛ የምርመራ ዘገባ ዘዴ በመጠቀም ከእስርቤት ያጠናቀረው

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደንና አስተዳደራቸውን የሚያጋልጥ ምስጢራዊ ድምፅ WT Media ከፍተኛ የምርመራ ዘገባ ዘዴ በመጠቀም ከእስርቤት ያጠናቀረው ቀርቧል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተቀነባበረ ሴራ የፖለቲካ እስረኛ ሆነናል የሚሉት የቀድሞው የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሚፈጸሙ አስተዳደራዊ በደሎችንና የሀብት ዝርፊያዎችን የሚያጋልጥ ምስጢራዊ ድምፅ ይፋ አድርገዋል።

WT Media በምስጢር ከፍተኛ የምርመራ ዘገባ ዘዴ በመጠቀም ከእስርቤት ያጠናቀረው መረጃ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በ አቶ ዳዊት እነዚህን ብልሹ አሠራሮች በማጋለጣቸውና በማስረጃ በመሞገታቸው፣ በአሁኑ ወቅት የ4 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት በዚሁ ሴራ መሆኑን ተናግረዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ዳዊት ገበየሁ በምስጢር ባወጡት የድምፅ መረጃ፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የሚመራው አስተዳደር ቅድሚያ ለሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ከመስጠት ይልቅ፣ ለቢሊዮን ብር የቅንጦት ፕሮጀክቶችና ለተደራጀ የሀብት ዝርፊያ ትኩረት መስጠቱን በዝርዝር አጋልጠዋል።

አቶ ዳዊት በንግግራቸው ላይ በግልጽ እንደተናገሩት፣ የክልሉ መንግሥት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መድቦ ስታዲየም ለመገንባት የሚያደርገው ጥረት በከፍተኛ ድርቅና የውሃ እጥረት በሚሰቃየው ሕዝብ ላይ የሚደረግ መቀለድ ነው።”100 ሚሊዮን ብር የማይሞላውን የውሃ ፕሮጀክት ትተህ በቢሊዮኖች ለስታዲየም ግንባታ የምታስበው ነገር እንደ አንድ ዜጋ ይሰማኛል” በማለት ርዕሰ መስተዳድሩን በፊት ለፊት እንደሞገቱ ገልጸዋል።

አቶ ዳዊት የክልሉ አመራር ዞኖችንና ሕዝቦችን አንድ እንዳይሆኑ በማጋጨትና በመከፋፈል የግል ሥልጣኑን ለማቆየት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል። “ዞኖች አንድ ሆነው ስለ ሰላምና ልማት ሲያወሩ ነው ለእኛ እፎይታ የሚሆነው፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሲተራመስ ማየት ለክልሉ ውርደት ነው” በማለት የአሁኑን አካሄድ ተችተዋል።

በተለይም በወላይታና በጋሞ ዞኖች መካከል ያለውን የቤት ግንባታ ሕጋዊነት አሠራር ልዩነት እንደ ማሳያ አንስተዋል። በክልሉ ውስጥ ለልማት ማኅበራት በሚል ስም ከካቢኔ ዕውቅና ውጪ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚሰበሰብ አቶ ዳዊት አጋልጠዋል።

ለጋሞ ልማት ማኅበር ተብሎ የተሰበሰበው 100 ሚሊዮን ብር እና ለስታዲየም ግንባታ የሚውለው አሸዋ ለሌላ ጥቅም መዋሉን “እጅ ከፍንጅ” መያዛቸውን በድምፅ ፋይሉ ላይ በምሬት ይገልጻሉ። እነዚህን ብልሽቶች በማጋለጣቸው ምክንያት ከርዕሰ መስተዳድሩና ከሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ መግባታቸውን አቶ ዳዊት ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን ከበደ አቶ ዳዊት በስብሰባዎች ላይ እንዳይገኙና ደብዳቤ እንዳይጽፉ ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን፣ ይህም በመጨረሻ ለ 4 ዓመታት የፖለቲካ እስራት እንዲዳረጉ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

በአቶ ዳዊት ገበየሁ የቀረበው ይህ ምስክርነት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለውን ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር እጦትና የተደራጀ የሙስና መረብ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይሄ የከፍተኛ አመራሩ ዘገባ የሚያመለክተው WT Media በየጊዜው የክልሉን ብልሽት በተመለከተ በተደጋጋሚ የሚያቀርባቸው ዘገባዎችን እውነተኝነት ያረጋገጠ ሆኗል።  የክልሉ መንግሥት ለእነዚህ ከባድ ክሶች የሚሰጠው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል WT Media ሂደቱን በቅርበት መከታተሉን ይቀጥላል።