“ራሱን ፋኖ የሚለው ታጣቂ ቡድን በአማራ ክልል ያደረሰው ውድመት፣ የህዝብ ሰቆቃና መፍትሔ” – በባህርዳሩ ፕሮፌሰር ሚኒሊክ ሸዋ እና በሐዋሳው ሰብዓዊ መብት ተሟጋች
የባህርዳር ዩንቨርስቲ መምህርና ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር ሚኒሊክ ሸዋ (ለደህንነታቸው ስም ተቀይሯል)፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ራሱን “ፋኖ” ብሎ ራሱን የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በአማራ ክልል ላይ ያደረሰውን ዘግናኝና “መራራ እውነት” በማለት የገለጹትን ዝርዝር መረጃ ለ WT Media አድርሰዋል።
ፕሮፌሰሩ ይህንን መረጃ ይፋ ያደረጉት፣ መላው የኢትዮጵያ ብሄሮችና ፖለቲከኞች በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ተረድተው፣ ለአማራ ህዝብ አጋርነታቸውን በማሳየት ይህንን ፅንፈኛ ቡድን በጋራ እንዲታገሉ ጥሪ ለማቅረብ ነው።
ፕሮፌሰር ሚኒሊክ ሸዋ በአማራ ክልል የተከሰተውን ሁለንተናዊ ውድመት በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ከፍለው አቅርበውታል።
1. የትውልድና ማህበራዊ አገልግሎቶች መፍረስ
A. የትምህርት መታወክ፦ ከ2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ከሚሊዮን በላይ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል። ቡድኑ ትምህርት መከልከልንና ማገትን እንደ መሳሪያ እየተጠቀመ ሲሆን፣ ተግባሩም ከቦኮሃራም/አል ሸባብ ጋር ይመሳሰላል።
B. የመሰረተ ልማት ውድመት፦ በርካታ የጤናና የትምህርት ተቋማት ወድመዋል ወይም ተዘርፈዋል። የመንገድ፣ የመብራትና የውሃ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ወይም ተዘርፈዋል።
C. የጤና ቀውስ፦ በኮሌራና በወባ ወረርሽኝ፣ በህክምና እጦት እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት የሚያልቀው የህዝብ ቁጥር በውል አይታወቅም።
2. ስርአት አልበኝነትና ሰብዓዊ መብት ጥሰት
A. የዜጎች ሰቆቃ፦ ህዝቡ በስርዓት አልበኝነት፣ በዕገታና በዝርፊያ መኖር ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል። ሴቶች የአስገድዶ መደፈር ሰለባ እየሆኑ ነው።
B. የእምነት ቦታዎች መደፈር፦ የዕምነት ቦታዎች በሽፍታ ተደፍረውና በጥገና ዕጦት ወደ ፍርስራሽነት እየተቀየሩ ነው።
C. ግድያና ማናናቅ፦ ከቡድኑ የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ ባለስልጣናትን፣ ሽማግሌዎችንና የተማሩ ሰዎችን መሳደብ፣ ማናናቅና ካልተስማሙ እስከ መግደል የሚደርስ እርምጃ መውሰድ የተለመደ ሆኗል።
3. የኢኮኖሚ ውድመትና የክልሉ መዳከም
A. የኢንቨስትመንት መፍሰስ፦ ኢንቨስትመንቶች ወድመዋል ወይም ስራ አቁመው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተበትነዋል።
B. ለወረራ መጋለጥ፦ የክልሉን በሽፍታ መዳከም እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ለድጋሚ ወረራ እየተዳረገ ነው።
4. የቡድኑ ማንነት፣ ግብና አራማጆች
ፕሮፌሰር ሚኒሊክ ሸዋ የዚህን “ክፉ ስብስብ” እና ደጋፊዎች ማንነት በሚል እንደሚከተለው ገልጸዋል፦
A. የቡድኑ ስብጥር፦ ቡድኑ የሃይማኖት አክራሪነት የተጫጫናቸው፣ ከእስር ቤት ያመለጡ አደገኛ ወንጀለኞች፣ የከዱ ወታደሮች፣ ስራ ያጡ ሰዎችና በዩቱዩብ ውትወታ ማሰቢያቸው የተሰለበ የገጠር ወጣቶች ስብስብ ነው።
B. ግብ፦ የቡድኑ ዋና ግብ ስልጣን (ንጉስነት) በመሆኑ፣ ስልጣን የሚያገኝ ከመሰለው የአማራ ህዝብ በሙሉ ቢያልቅ ግድ የለውም። “ነፃ አውጪ” በሚል ሽፋን የገንዘብ ችግሩን በዝርፊያ ይሞላል።
C. የውጭ አራማጆች፦ መቀመጫቸውን ውጭ ሀገር በማድረግ በዩቲዩብ አሉባልታና ውሸት ችግሩን የሚያባብሱ፣ ፋኖ ከሚዘርፈው ገንዘብ በደርዘን የሚቆጠር ዶላር የሚያገኙ (እንደ ጋዜጠኛ መሳይ መሠለ፣ ደረጃ ሀበቴ፣ ሀብታሙ፣ ፋሲል ወዘተ ያሉ) እና መንጋው ሚሊዮን ህዝባችንን ታይቶ ተሰምቶ ወደማይታወቅ መከራ ውስጥ አስገብተውታል።
አሁን ክልሉ ከሞላ ጎደል ወደ ድንጋይ ዘመን ተመልሶ የገሃነም ምሳሌ ሆኗል ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ሰው እየገደሉና ሀብት እያወደሙ “ፈጣሪ ይረዳናል” ማለት ግብዝነት መሆኑን ገልጸዋል።



በክልሉ ውስጥና ውጪ የሚኖረው የአማራ ማህበረሰብ የጥቃት ተጋላጭነት ተባብሶ መቀጠሉን ጠቅሰው፣ መላው ኢትዮጵያዊ ይሄንን ተረድቶ ፅንፈኛ ቡድኑን በጋራ እንዲታገል ፕሮፌሰር ሚኒሊክ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
WT Media በፕሮፌሰር ሚኒሊክ ሸዋ የቀረበው መረጃ መነሻ አስተያየት እንዲሰጥበት አንድ የሐዋሳ ዩንቨርስቲ መምህራንና ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሲገልፁ “ይሄ የሚያሳየው የፖለቲካ ትግልን ሳይሆን፣ በአማራ ክልል እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ዘግናኝ የህዝብ ሰቆቃ ነው” ብለዋል።
ምሁሩ ሁኔታውን ሲጠልፁ “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ወደ ጨለማ ሲገፉ፣ እናቶች የአስገድዶ መደፈር ሰለባ ሲሆኑ፣ እና ወንድም ወንድሙን በደም ገንዘብ እንዲገድል ሲበረታታ ዝምታን መምረጥ ለጥፋቱ ተባባሪ መሆን ነው” በሚል ገልጸዋል።
አክለውም ሚዲያዎችን ፣ ጋዜጠኞችንና የመብት ተሟጋቾች የአማራ ክልል ህዝብ እየደረሰበት ያለውን መከራ ያለ አድልዎና ሳይሸፋፍኑ ለዓለም ማሳወቅ የሙያዊ ግዴታችሁ ነው። የንጹሃን ጩኸት ከጥላቻ ፖለቲካና ከአሉባልታ በላይ ሊደመጥ ይገባል በሚል አሳስበዋል።
የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እንደ አንድ ትልቅ ሰብዓዊ ቀውስ ተመልክተው፣ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግና ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሜርካ የ”Tier III” የሽብር ፍረጃዎች በተግባር የሚታዩትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል።
ምሁሩ ጨምረውም ሰላም ሁልጊዜም አማራጭ የሌለው ብቸኛ መንገድ መሆኑን ሳይሰለች በመፈለግ፣ ህዝብን ከዚህ ታይቶ የማይታወቅ ሰቆቃ የሚያወጣ ልዩ ብሄራዊ ስትራቴጂ እንዲቀርብ አሳስበዋል።
የክልሉን ደህንነት ማስጠበቅ፣ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ መገንባትና ትውልዱን ወደ ትምህርት ገበታ መመለስ የመንግስት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል በሚልም ጠቁመዋል።
በአጠቃላይ፣ የአማራ ህዝብ ከዚህ የገሃነም አዙሪት ወጥቶ ወደ ቀድሞ ስልጣኔውና ሰላሙ እንዲመለስ፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተደመረ ጥረትና አጋርነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ያስፈልጋል በሚለው የባህርዳር ዩንቨርስቲ ምሁር ፕሮፌሰር ሚኒሊክ እና የሐዋሳ ዩንቨርስቲ መምህርና ሰብዓዊ መብት ተሟጋች አፅንኦት ሰጥቶት ጥሪ አቅርበዋል።
ማሳሰቢያ፦ WT Media በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በመንግሥት ሚዲያዎች ትኩረት ያላገኙ ለተጨቆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ የቅድሚያ ቅድሚያ የምንሰጥ ሲሆን እውነትን፣ ሀቅንና ፍትሕን መሠረት በማድረግ፣ የመረጃ ሰጪዎችን ምስጢርና ደኅንነት በመጠበቅ በሌሎች ሚዲያዎች የማይሰሙ የጭቁኖች ድምፅ ዘውትር እዚሁ ይሰማልና ስለአብሮነታችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው! የእናንተው የጭቁኖች አገልጋይ ነን🙏
Voice of Marginalized Community – WT Media