ዲስትሪክቱ በ2013 ዕቅድ አፈፃፀምና በ2014 በጀት አመት መነሻ ዕቅድ ዙሪያ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ጉታራ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል፡፡
በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የሶዶ ዲስትሪከት ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ ተመስገን ያይና እንዳሉት በ2013 በጀት አመት በሁሉም ተግባራት ከዕቅድ በላይ መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡
አቶ ተመስገን አክለው በቁጠባ አሰባሰብ በብድር ስርጭትና በብድር አመላለስ ከዕቅድ በላይ መፈፀሙንና ውዝፍ ዕዳ ከማስመለስ ጋር ተያይዞ የሚታየውን ክፍተት ለማረም በርካታ ቅንጅታዊ ሥራዎች መፈፀማቸውንና ይህም በ2014 በጀት አመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በ2013 በጀት አመት 1 ቢሊዮን 197 ሚሊዮን 473 ሺህ 672 ብር አጠቃላይ ቁጠባ ከተለያዩ ደንበኞች መሰብሰብ መቻሉንና አፈፃፀሙም 162% መድረሱን ገልፀዋል፡፡
በብድር ስርጭት 430 ሚሊዮን 917 ሺህ 880 ብር እና በብድር አመላለስ 379 ሚሊዮን 922 ሺህ 974 ብር ማሳካት መቻሉንና አፈፃፀሙ 166% እና 152% በቅድመ ተከተላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ተቋሙ በ2014 ዓ/ም ወደባንክ ደረጃ የሚያድግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለደንበኞቹ ሰፊ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የጠቆሙት አቶ ተመስገን ሁሉም የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጀመሩትን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንዲቀጥሉና የሚመለከታቸው አካላትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዲስትሪክቱ ደንበኞች ቁጠባን ባህል እንዲያደርጉና የተበደሩትን ገንዘብ በገቡት ውል መሰረት በጊዜ በመመለስ የራሳቸውን ዕድገት እና የተቋሙን ራዕይ ዕውን ለማድረግ በዓላማ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
አቶ መተኪያ ዳካ በዲስትሪክቱ የዳሞታ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ ፈለቀ ፋንታ የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ እና አቶ ፍቅሬ አጫ የአረካ ከተማ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት በ2013 በጀት ዓመት በቁጠባ አሰባሰብ፣ በብድር ሥርጭትና ብድር አመላለስ ከዕቅድ በላይ የፈጸሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራም ከሚሰራጭ ብድር ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመቅረፍ በተሰራው ቅንጅታዊ አሰራር የተሸለ ውጤት መመዝገቡን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጆች በ2014 በጀት ዓመትም የተሸለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን መዘጋታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክWolaita Timesme/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 27/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
