በዎላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማና አከባቢው ላይ የኔትወርክ አገልግሎት ዘገምተኛ በመሆኑ ነዋሪዎችና ተቋማት ለተለያዩ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑ ተገለፀ
በከተማዋና አከባቢው ላይ የመደበኛ የእጅ ስልክ አገልግሎት ጨምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሁኔታ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ለችግር መጋለጣቸውንም ተናግረዋል።
የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከነዋሪዎቹና ተቋማት በደረሰው የቅሬታ ጥቆማ መሠረት በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ዙሪያ በከተማዋ ተገኝቶ የቅሬታ አቅራቢዎች ሀሳብ አሰባስቧል።
በጉዳዩ ዙሪያ WT ሚዲያ ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በከተማዋ መደበኛ የእጅ ስልክ አገልግሎት ጨምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ኔትወርክ በጣም ዝቅተኛና ዘገምተኛ በመሆኑ አገልግሎቱን በተገቢው ማግኘት ባለመቻሉ ቅሬታ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በከተማዋ የሚገኘው የቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሚገኝበት አከባቢ የመደበኛ የስልክ አገልግሎት፣ የእጅ ስልክና የWif አገልግሎት ጭምር አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ በተቋሙ ስራ ላይ ከፍተኛ ጉዳትና ጫና እያደረሰ መሆኑንም ሚዲያው በቦታው ተገኝቶ ለማረጋገጥ ችሏል።
የቦዲቲ ከተማ በዞኑ ውስጥ በርካታ የንግድ ተቋማት፣ ፋብሪካዎች፣ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በርካታ የስልክና የኢንተርኔት ተጠቃሚ የሚገኝባት ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ሶዶ በስተሰሜን በኩል በ18 ኪ.ሜ ርቀት የሚትገኝ ከተማ መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን የዎላይታ ሶዶ ድስትሪክ በዎላይታና አከባቢው ከቅርብ ወራት በፊት የአራተኛ ትውልድ ኔትወርክ ዝርጋታ ተግባራዊ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ከቦዲቲ ከተማ ነዋሪዎችና ተቋማት ለተነሳው ቅሬታ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት እያደረገ ያለው ሲሳካ መረጃውን የሚያቀርበው ይሆናል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 28/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹