በዎላይታ ዞን ውስጥ ከሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች መካከል ተማሪዎችን ውጤታማ በማድረግ የሚታወቀውና 15ኛ ዓመት የምስረታ ስነስራዓት ያከበረው ካምፎውርድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በወረዳ ደረጃ የተማሪዎችና የወላጆች ቀን በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

በተማሪዎች ካርድ አሰጣጥ፣ የተማሪዎችና የወላጆች ቀን አከባበር ስነስርዓት ላይ የተለያዩ የመንግስት ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የተማሪዎች ወላጆችና ሌሎች የአከባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ኮምፎወርድ የመጀመሪያ ደረጃ የግል ትምህርት ቤት ከመዋለ ህፃናት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ በወረዳዋ ጥራት ያለውን ውጤታማ ትምህርት ለተማሪዎች በመስጠት በአከባቢው ትምህርት ዘርፍ የራሱን ሚና እየተጫወተ የሚገኝ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በወረዳዋ ካምፎውርድ አንደኛ ደረጃ የግል ትምህርት ቤት ጨምረው 30 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ።

ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1

በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

Wolaita Times, 29/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹