የዎላይታ ዞን ለመከላከያ ሠራዊት ከ17 ነጥብ አራት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በአይነትና በገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
አሸባሪው ህውሃት ቡድን በሀገራችን ህዝብ ላይ የደቀነውን የህልውና አደጋ በመረዳት ግንባር ላይ ለሚገኘዉ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የሚሆኑ ድጋፍ ሲያሰባስብ መቆየቱ ይታወሳል።
የሀብት አሰባሰቡ በጥሬ ገንዘብ 14,083,351/አስራ አምስት ሚሊዮን ሰማኒያ ሶስት ሽህ ሶስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር/ እና በዓይነት 3,400,000/ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ሽህ ብር /መሰብሰቡን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ጠቁመዋል፡፡
በአጠቃላይ በዞኑ በዚህ ዙር በተደረገው ድጋፍ በአይነትና በጥሬ ገንዘብ 17 ሚሊዮን 4 መቶ 83 ሺህ 3 መቶ 51 ብር የሚገመት ሀብት ተሰብስቦ ወደ ማዕከል መደረሱን የዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል አስታዉቀዋል፡፡
ድጋፉ በዞኑ ከሚገኙ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች፣ ከተለያዩ ህብረሰተብ ክፍል፤ የመንግሥትና የግል ተቋማት እና ከመንግስት ሠራተኞች የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የዎላይታ ህዝብ እስካሁን ድረስ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ያደረገዉን ድጋፍ አቶ ሳሙኤል ምስጋና አቀርበው በቀጣይ ጊዜያትም ህዝቡ ድጋፋውን አጠናክሮ እንዲያስቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚያስፈልገውን ሁለንታናዊ ድጋፍ በቀጣይነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዎላይታ ዞን ሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ መጠቆሙን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 29/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹

