በወቅቱ ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ኃይለማርያም ፍርድቤት ቀርበው የምስክርነት ቃል እንዲሰጡ የሚያዝዝ የፍርድቤት ትዕዛዝ ወረቀት የተቀበለው የፅህፈት ቤት ኃላፊ በህመም ምክንያት ማድረስ አለመቻላቸው በመገለፁ የፈደራል ከፍተኛ ፍርድቤት መጥሪያውን ያላደረሰው “ታስሮ ይቀርብ” ያለውን ውሳኔ እንዲቀር አድርጓል።
ፅህፈትቤቱ ለአቶ ኃይለማርያም መጥሪያ ማድረሳቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርቡና ምስክሩ(አቶ ኃይለማርያም) በስራ ምክንያት በውጭ ሀገር በመሆናቸው ወደ ሀገር ውስጥ የሚመለሱበትን ቀን በማረጋገጥ ለፍርድ ቤቱ እንዲያሳውቅ ለፅህፈት ቤት ኃላፊ ተነግረዋል።
የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዛሬው ዕለት ሰሞኑን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ታስረዋል ተብለው የሚወራው ወሬ ውሸት መሆንና በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ከተለያዩ ጫና ወጥታ የለውጥ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን የምታደርገውን ጥረት ከመንግስት ጎን በቅርበት እየተከታተሉና የበኩላቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውንም አረጋግጦ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 29/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹

