በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሦስተኛ ዙር የመሰረታዊ ውትድርና ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመርያ መርሀ-ግብር ተከናወነ፡፡
በስልጠና ማስጀመርያ መርሀ-ግብር ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ስልጠናው መጀመሩን ያበሰሩት በኢፌዴሪ የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጁንታው የህውሀት ቡድን በፈፀመብን ክህደት በሰራዊታችንና በህዝባችን ላይ የተቃጣውን ጥቃት በመመከት በህግ ማስከበር ዘመቻው የጁንታውን ሀይል በመደምሰስ ሀገርን የማዳን ተልዕኮ በጀግንነት በመፈፀም ላይ የምንገኝ ሲሆን እናንተም በሀገራችንም ላይ የሚቃጣውን ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከልና ህገ-መንግስቱን ለማስከበርም ሆነ ለመጠበቅ ወደ ተቋሙ በመቀላቀላችሁ ኩራት ሊሰማችሁ ይገባል ብለዋል፡፡
በማሰልጠኛው ውስጥ በሚኖራችሁ ቆይታ ከምንም በላይ የሚያስተሳስራችሁ ሀገራዊ ማንነት አንድነትና ኢትዮያዊነትን አጎልብታችሁ መውጣት አለባችሁ ብለዋል፡፡
በስልጠናው ማስጀመርያ መርሀ ግብር ላይ የማሰልጠኛው ትምህርት ቤት ስታፍ የሰራዊት አባላት ፣ ብርጌድ አመራሮች እና አሰልጣኞች የተገኙ ሲሆን ፣ የምስራቅ ዕዝ ኦርኬስትራ ለምልምል ሰልጣኞች የተለያዩ ሀገራዊ ይዘት ያላቸውን ጣእመ ዜማዎችን አቅርቧል ሲል መከላከያ ሰራዊት ገልጿል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 30/11/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹
