የከተማው ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት በበኩሉ በከተማዋ ማንኛውንም ከህግ አግባብ ውጭ የተገነቡ ቤቶች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ እጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ሰሞኑን በቦዲቲ ከተማ የተለያዩ ግለሰቦች ለንግድና ለሌላ ስራዎች በተገነቡ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ፍትሀዊነት የጎደለው ነው ስሉ ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅሬታ ተናግረዋል።
የፈረሱት ቤቶች በአብዛኛው ከአምስት አመት በፊት የተገነቡ ሲሆን የተለያዩ ንግድ ስራ የጀመሩና ግብር የሚከፍሉ እንደሆነ ገልፀው ምንም አይነት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ፈርሰዋል ስሉም አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
እየተወሰደ ያለው እርምጃ ሁሉንም ተመሳሳይ ግንባታ ያካሄዱ አካላትን ያማከለ አይደለም ያሉት አሰተያየት ሰጪዎቹ እየተደረገ የሚገኘው ነገር ፍታዊነት የጎደለውና በዚያ ቤት ለአመታት ሰርተው የዕለት ጉርሳቸውን አግኝተነው የሚኖሩ ሰዎችን የሚጎዳና መፍትሄ አቅጣጫ ያልሰጠ እርምጃ ነው ስሉም ነዋሪዎቹ ቅሬታ አክለው ተናግረዋል።
የከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፅ/ቤት ሥራ አስከያጅ አቶ መስፍን ኤጃሞ በበኩላቸው በከተማዋ ከማስተር ፕላን ውጭ በየመንገድ ዳር በህገወጥ መንገድ የተገነቡ የጥላ ሼድ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ስሉ ገልጸዋል።
ይህም በህገወጥ መንገድ ግንባታ በማከናወን በተለያዩ ስራዎች የተሰማሩ ግለሰቦች እንዲያነሱ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥተው ወደ እርምጃ መገባቱንም ተናግረዋል።
የከተማውን ዕድገት በተገቢው ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች ላይ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ ያለ ነው በማለት የህገወጥ ቤቶች ግንባታና የመሬት ወረራዎችን ለመከላከል በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።
አቶ መስፍን ከተማዋን ለማልማት ለተጀመሩ ሥራዎች 75 ከመቶ የሚሆኑ ህገወጥ ቤቶቹን አፍርሰናል ይበሉ እንጅ በከተማው ከማስተር ፕላን ውጭ የተገነቡ በርካታ ያልፈረሱ ተመሳሳይ ህገወጥ ቤቶች በየመንገዱ ዳር መኖራቸውን የዎላይታ ሚዲያ በከተማዋ ቅኝት ባደረገበት ወቅት ለመመልከት ችለዋል።
በቀጣይነትም በጉዳዩ ዙሪያ የWT ሚዲያ ተከታትሎ ዘገባ ይሰራል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 01/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹


