GridArt_20260610_194034432

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋሞ ልማት ማህበር (ጋልማ) ውስጥ የተቀሰቀሰውን ውዝግብ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ዶከተር ዋኖ ዋሎሌ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ታውቋል።

​ከሀዋሳ ከተማ ተይዘው በዎላይታ ሶዶ በኩል ወደ አርባምንጭ የተወሰዱት ዶክተር ዋኖ ዋሎሌ በማህበሩ ውስጥ ካለ የገንዘብ ብዝበዛ ጥቆማ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ቢደረግም ይፋዊው የእስር ምክንያት ግን በሙስና ወንጀል መጠርጠራቸው እንደሆነ ታውቋል።

ግለሰቡ መኖሪያ ቤታቸው ከሚገኝበት ከሀዋሳ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሎ ከተያዙ በኋላ በቀጥታ ወደ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ተወስደው ለሁለት ቀናት በእስር ላይ እንዲቆዩ ተደርጎ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ለሁለት ቀናት ከታሰሩ በኋላ ትናንት ማመሻውን ወደ አርባምንጭ ከተማ መወሰዳቸው የ WT Media ምንጮች አረጋግጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጥቂት ወራት በፊት አቶ ዋኖ ከስልጣን መባረራቸውን ተከትሎ የልማት ማህበሩን ስራዎች እንዲመሩ አዳዲስ አመራሮች መመደባቸው ይታወቃል።

​ዶክተር ዋኖ ዋሎሌ በማህበሩ የገንዘብ ብዝበዛን አጋልጠዋል በሚል ከመኖሪያ ቤታቸው መወሰዳቸውን ተከትሎ የእስሩ ሂደት አሁንም በአከባቢው ከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ፈጥሯል።

ከአርባምንጭ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት በተቋሙ ውስጥ ካሉ የፋይናንስ እና የአሰራር ግድፈቶች እንዲሁም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው።

​በሌላ በኩል ከርዕሰ መስተዳድሩ ከአቶ ጥላሁን ከበደ ጋር የነበረውን በዝርፍያ ባለመተባበር አለመግባባት እና ህገ-ወጥ ትዕዛዞችን አለመቀበልን ተከትሎ የተፈጸመ እስራት ነው በሚል በአካባቢው አመራሮች ዘንድ ከፍተኛ ክፍፍል መፍጠሩንም ከመረጃ ለማጣራት ችለናል።