የዎላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ እግር ኳስን ከ2008-2010 የውድድር ዓመት ድረስ በሀዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ቤት፣ 2011 የውድድር ዓመትን በአርባምንጭ እግርኳስ ክለብ እንዲሁም 2012 እና 2013 የውድድር ዓመትን በድጋሚ በሀዲያ ሆሳዕና እግርኳስ ክለብ የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች የነብረውን በረከት ወልደዮሐንስ ለሁለት ዓመት ኮንትራት አስፈርሟል።
በተጨማሪም የእግርኳስ ህይወቱን በዎላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች፣ ከ20 ዓመት በታች እንዲሁም በዋናው የእግር ኳስ ክለብ በግብ ጠባቂነት ሥፍራ ተጫዋችነት የሚታወቀውን ቢንያም ገነቱን ለሁለት ዓመት ኮንትራት ማስፈረሙን ከክለቡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዝርዝር ወቅታዊ፣ ትኩስ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት
www.wolaitatimes.com.et
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/wolaitatime/
ቴሌግራም፦
https://telegram.me/Kiikiya
ዩቲዩብ፦
https://m.youtube.com/channel/UCQy9hoOijiE8FStts2SmtXw?noapp=1
በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
Wolaita Times, 01/12/13 E.C , Sodo, Ethiopia🇪🇹

